ስለኢድ አል -አድሃ አምስቱ መሠረታዊ ነገሮች ፡-

5

1 ኛ -የእርድ ( የመስዋዕት ) በዓል የሆነው ኢድ አል አድሃ በእስልምና እምነት ከሚታወቁት ታላላቅ በዓላት አንዱ ነው፡፡ አንደኛው ትልቅ ዓመታዊ በዓል የረመዳን ወር ጾምን ተከትሎ የሚመጣው ኢድ አል- ፊጥር ነው፡፡

2ኛ-ኢድ አል አድሃ አላህ የኢብራሂምን የእምነት ጽናት ለመፈተን በስተእርጅና ያገኘውን አንድ ልጁን ለክብሩ እንዲሰዋለት የፈተነበትን ሁኔታ የሚዘከርበት ዕለት ነው፡፡

ኢብራሂም የአምላኩን ትዕዛዝ ተቀብሉ ልጁን ወደመሰዊያው ባቀረበው ጊዜ አላህ በመንፈስ ቀርቦ በልጁ ፈንታ በግ እንዲሰዋለት ማድረጉን በቅዱስ ቁርአን፣ በመጽሀፍ ቅዱስ እና በአይሁዶች ቶራህ ላይ ተጽፏል፡፡

3ኛ-ኢብራሂም የአምላኩን ፈቃድ ለመፈጸም የቀረበለትን ፈተና ተቋቁሞ በበግ መስዋዕትነት መጠናቀቁን ለማስታወስ የሙስሊም እምነት ተከታዮች ሙክት አሊያም ከብት በማረድ ለድሆች የሚያከፋፍሉበት ስርዓት የበዓሉ አንድ አካል ነው ፡፡

4ኛ- ለአራት ቀናት በሚከበረው በዚህ የኢድ አል አድሃ ሃይማኖታዊ ስርዓት አቅሙ ያላቸው ሙስሊሞች ወደመካ የሃጂ ጉዞ ያደርጋሉ፡፡በሃጂ ጉዞው በየዓመቱ ሁለት ሚሊዮን አቅሙ ያላቸው አማኞች ይሳተፋሉ፡፡

5ኛ-በሙስሊሙ ዓለም በየዓመቱ አዲስ ጨረቃ እንደታየች በዓሉ መከበር ይጀምራል፡፡

ኢድ ሙባረክ ! !

አዲስ ዘመን ነሐሴ 5 /2011