ቻይና በኢንቨስትመንት የባልካን አገራትን ተቆጣጥራለች

21

እ.አ.አ 2009 ጥቅምት ወር ላይ በቡልጋሪያ በምትገኘው ትንሿ ሎቪች ከተማ የቻይና ልዑካንን ሞቅ ባለ ሁኔታ መቀበሏ ይታወሳል። ዢ ቺንፒንግ ቀጥሎ ደግሞ ምክትላቸው በአውሮፓ ጉብኝት አድርገው የነበረ ሲሆን በጉብኝቱም ከአውሮፓ አገራት የተለያዩ ልምዶች ቀስመዋል። በፕሬዚዳንቶቹ ጉብኝት ወቅት በቡልጋሪያ ሎቪቭ ከተማ ውስጥ ከሚገኙት ሊቴክስ ኮሜርስና ከግሬት ወል ሞተርስ ድርጅቶች ጋር የትብብር ስምምነት ተደርጓል። ድርጅቶቹ በቻይናውያን ባለሀብቶች የተያዙ ናቸው። ይህ ሁኔታ ቻይና በባልካን አገራት ውስጥ ያላትን የንግድ ተሳትፎ እንድታሳድግ አግዟታል።

በሎቪች የሚገኙት የቻይና አምራች ድርጅቶች እ.አ.አ 2017 ላይ ከፍተኛ የሆነ ውጤት ቢያስመዘግቡም የቻይናን የኢንቨስትመንት ፍላጎት ያረኩ አልነበረም። ከአስር ዓመት በኋላ የባልካን አገራት መሪዎች ከቻይና ጋር በኢንቨስትመንት ለመተሳሰር ዢ ቺንፒንግን በማግኘት በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ። በአሁን ወቅት አሜሪካ ከቻይና ጋር የንግድ ጦርነት ውስጥ የምትገኝ ሲሆን ምዕራባውያን ደግሞ የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያ ከሆነው ሂዋዌ ኩባንያ ጋር አብረው ለመስራት ፍላጎት እያሳዩ ነው። የደቡብ ምስራቅ አውሮፓ አገራት ደግሞ ከቻይና ጋር ኢንቨስትመንት ለመፈራረም መንገድ ጀምረዋል። የባልካን አገራት ደግሞ በመንገድ፣ በድልድይ፣ በኤልክትሪክ ሃይል ግንባታ እና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አብሮ ለመስራት ፍላጎታቸውን እያሳዩ ነው።

እ.አ.አ 2012 ሚያዚያ ወር አንድ ዓመት በፊት የቻይና ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ዢ ቺንፒንግ 16 ፕላስ አንድ የሚል የኢንቨስትመንት እቅድ ያወጡ ሲሆን እቅዱ ቻይና በምስራቅ አውሮፓ ከሚገኙ ከአስራ አንዱ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት እንዲሁም አምስት ከምዕራብ ባልካን አገራት ጋር ለመስራት የሚያስችል ነው። በዚህም የባልካን አገራት ያለምንም ማመንታት የእቅዱ አካል መሆን ችለዋል። እ.አ.አ 2018 ላይ ሶሪያ ስብሰባውን ያዘጋጀች ሲሆን የዚህን ዓመት ደግሞ በክሮሺያ ዱብሮፊንኪ ከተማ ተካሂዷል። ባልጋርዴና ቡሻረስት ላለፉት ዓመታት ስብሰባውን አዘጋጅተው ነበር። ዘግይታም ቢሆን ግሪክ ወደ ፎረሙ የተቀላቀለች ሲሆን አጠቃላይ ቡድኑ 17 ፕላስ አንድ መሆን ችሏል።

በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት የባልካን አገራት ከፍተኛ ባለስልጣኖች ወደ ቤጂንግ ለጉብኝት ተጉዘዋል። እ.አ.አ 2019 ሚያዚያ ወር ላይ የሰርቢያው ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ቪውሲስ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ጋር የተገኙ ሲሆን ከሳቸው ቀጥሎ ደግሞ የግሪኩ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲ ፂፕራስ ከፕሬዚዳንት ዢ ቺንቢንግ ጋር ውይይት አድርገዋል። በግንቦት ወር ደግሞ የግሪኩ ፕሬዚዳንት ፕሮኮፒስ ፓቮሎፖውሎስ ቤጂንግ ተጉዘው ነበር። በሐምሌ ወር ደግሞ የቡልጋሪያው ፕሬዚዳንት ሩመን ራዴቭ በቤጂንግ ይፋዊ ጉብኝት አድርገዋል።

የባልካን አገራት ከቻይና ጋር በኢንቨስትመንት ለመተሳሰር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አብዛኛው ውስጥ ለውስጥ ነው። በአውሮፓ ህብረት ውስጥ የሚገኙ አገራት የቻይናን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በአይነቁራኛ እየተከታሉት ሲሆን ቻይና የተለያዩ እቅዶችን በማውጣት የምታደርገውን የኢንቨስትመንት መስፋፋት እንድትቀንስ ጥረት ጀምረዋል።

የአውሮፓ አገራት ሩስያ ላይ ትኩረት በማድረጋቸው ቻይናን መቆጣጠር ባለመቻላቸው ቻይና የባልካን አገራትን ልትቆጣጠር ችላለች። ምዕራብ ባልካን አገራት በቻይና እዳ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከእዳው ለመላቀቅ ሰፊ ጊዜ ይፈልጋሉ። ሩስያ በዛልፊክ ወንድማማች ቡድን ስም ፍላጎቷን ለማሳካት ጥረት እያደረገች ሲሆን ምዕራባውያንን ለመፎካከር ጠቅሟታል።

በተጨማሪም ሩስያ የተጣለባትን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ለማርገብም ረድቷታል። ቻይና በተለያዩ አገራት ባላት ኢንቨስትመንት 12 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ጂዲፒ በዓመት ታገኛለች። ከተገኘው ጂዲፒ ሶስት በመቶው ቻይና በኢንቨስትመንት ወደ ባልካን አገራት ትመድበዋለች። በአብዛኛው የሚመደበው በጀት የቻይና መሠረተ ልማት ኩባንያዎችን በሚጠቅሙ ብድሮች ላይ የተመሠረተ ነው። ሁለት ሦስተኛውን ከሚይዘው የአውሮፓ ህብረት ድጋፍ ሲታይ በጣም ከፍተኛ ነው። እ.ኤ.አ. በ2013 ይፋ የተደረገው ትልቁ የመንገድ ግንባታ በቻይና ብድር ከተጀመረ በኋላ የአውሮፓ አገራት የብድር እዳ እየጨመረ ይገኛል።

የተወሰኑ የእዳ ገንዘቦች ለቻይና እየተመለሱ ሲሆን በተለይ በባልካን በሚገኙ የብረት ማቅለጫ ፋብሪካዎች ውስጥ ቻይና በአክሲዮን እየገባች ትገኛለች። በዚህም ሰርብያ የውጭ ንግድ እንቅስቃሴዋ ከስድስት ወደ አስራ ሁለት እንዲያድግ አድርጎታል። የቻይና ኤግዚም ባንክ ብድር የሰጠው ባልጋራድንና ቡዳፔስትን የሚያገናኘው የባቡር መንገድ እድሳት በአካባቢው የቻይና ተሳትፎ ምን ላይ እንደደረሰ ያሳያል። ግንባታውን የሚያከናውነው የቻይና ኮሙዩኒኬሽን ኮንስትራክሽን ድርጅት ሲሆን አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረግበታል።

የሰርብያ መንግስት ከቻይና ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን ለመግዛት ድርድር እያደረገ ሲሆን የግዥ ስምምነቱ ከቴክኖሎጂ ሽግግር አኳያ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተነግሯል። ሰርብያን የጦር ሃይላቸውን የማጠናከር የረጅም ጊዜ እቅድ አላቸው። ቡልጋርዴ ከቻይና የፊት መለያ ሶፍትዌር በቅርቡ ገዝታለች። በቅርቡ በቻይና ጉብኝት ያደረጉት የቡልጋሪያው የውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትሩ ናቦጅሳ ስቴቫኖቪክ የፖሊስ ስልጠናና ወታደራዊ ልምምድ ከቻይና ጋር ለማድረግ ተስማምተዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ቻይና ከባልካን አገራት ጋር ከእ.አ.አ 2005 እስከ 2016 ድረስ ያደረገችው የንግድ ልውውጥ አንድ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ዶላር ደርሷል። ሰርብያ ለቻይና የባልካን አገራት መግቢያ በር ሆና እያገለገለች ትገኛለች። የቻይናና የሰርብያ ትብብር እስከ ምን ድረስ እንደሚጓዝ የሚታወቅ ነገር የለም። ነገር ግን የሰርብያው ፕሬዚዳንት በሁለት መቀመጫ ላይ ሆነው እየሰሩ ሲሆን ይህም ማለት ከቻይና ጋር ካላቸው ግንኙነት ውጪ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚነት ሚና አላቸው። በአሁን ወቅት ሰርቢያ በምዕራባውያንና በሩስያ መካከል እየተወዛወዘች ትገኛለች።

የሰርብያ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ቻይና ከፍተኛ የሆነ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በሌሎች ባልካን አገራት በተለይ በመሰረተ ልማትና በሐይል አቅርቦት እየተሳተፈች ትገኛለች። ከእ.አ.አ 2009 ጀምሮ የቻይና ኩባያዎች ዋናውን የግሪክ ወደብ የሆነውን ፔሩሱ ከማንቀሳቀስ አልፈው በባለቤትነት እያስተዳደሩት ይገኛሉ። እስከ እ.አ.አ 2017 የቻይና ኩባንያዎች የቴሳሎኒኪ ወደብን ተቆጣጥረውታል።

እ.አ.አ 2013 ላይ የአውሮፓ ህብረት አባልነትን የተቀላቀለችው ክሮሺያ በቻይና የግንባታ ኩባንያዎች ሁለት ነጥብ አራት ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ድልድይ ተገንብቶለታል። ድልድዩ የፔልጄሳክ ፔንሱዌላ እና የኮማርና ገጠሪቱን ክፍል የሚያገናኝ ነው። የድልድይ ግንባታው ፕሮጀክት የሁለትዮሽ ጥቅምን ያስከበረ ነበር። የመጀመሪያው ጥቅም ኔውም ባህረሰላጤን ከቦስንያና ሄርዜጎቪንያ ጋር በማገናኘት የንግድ ልውውጥ እንዲፋጠን ያደርጋል። ሁለተኛው ደግሞ የድልድዩ ግንባታ በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ የተሰራ በመሆኑ ሲሆን የቻይና ኮንስትራክሽን ድርጅቶች ከድልድይ ግንባታ 396 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት ችለዋል።

ቻይና በሞንቴኔግሮና በሰሜን መቄዶንያ እየተሰሩ በሚገኙ የመንገድ ግንባታዎች ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ እደረገች ትገኛለች። በቱዝላ፣ በቦስንያ እና ሄርዜጎኖቪያ ውስጥ ቻይና ከኤግዚም ባንክ በተገኘ 777 ሚሊዮን ዶላር ብድር የውሃ ማጣሪያ እየገነባች ትገኛለች። ይህ የግንባታ እንቅስቃሴ በቅርቡ የተጀመረ ሲሆን በዋነኝነት በባልካን አገራት ፌዴሬሽን ውስጥ ፖለቲካዊ ጥቅም ለማግኘትና ለቀጣይ ፕሮጀክቶች ፈቃድ ለማግኘት ያለመ ስራ ነው።

ከውሃ ማጣሪያ ፕሮጀክቱ ግንባታ ሶስት የቻይና ኩባንያዎች እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ሁኔታው ፖለቲካዊ ሁኔታ ውስጥ ገብቷል። በዚህ ወቅት ቻይና የቦስንያን ባለስልጣናት በገንዘብ በመደለል የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት ማስቆም ችላለች። ቡልጋሪያ በተመሳሳይ በሐይል ዘርፍ የቻይናን ኢንቨስተሮች እየሳበች ትገኛለች። በተጨማሪም የቻይና ብሔራዊ የኒውክሌር ኮርፖሬሽን በቡልጋያ የኒውክሌር ማበልፀጊያ መገንባት ይፈልጋል።

አሁን እንደሚታየው ቻይና በባልካን አገራት ውስጥ የኢንቨስትመንት ተሳትፏዋን በማሳደግ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ማሳረፍ ትፈልጋለች። ነገር ግን በመካከለኛም ይሁን በአጭር ጊዜ ውስጥ ቻይና በአገራቱ የውስጥ ደህንነት ውስጥ እጇን የምታሳርፍበት መንገድ የላትም።

ነገር ግን ቻይና በባልካን በኢኮኖሚ ዙሪያ ተፅዕኖ ፈጣሪነቷን አሳይታለች። በሰሜን መቄዶንያ ውስጥ የቻይና የውጭ ፖሊሲ ባለሙያ የሆነው አናስታስ ቫንጌሊ እንደሚናገረው፤ የባልካን አገራት ከቻይና ጋር በኢንቨስትመንት የመተሳሰር ፍላጎት አላቸው። አውሮፓ ህብረት ከቻይና ጋር ከመወዳር ይልቅ በትብብር እየሰራ ይገኛል። መረጃውን ያገኘነው ከአልጀዚራና ቢቢሲ ነው።

አዲስ ዘመን ጳጉሜ 4/2011

መርድ ክፍሉ