ወጣቶች ስለ አዲሱ ዓመት ምን ይናገራሉ?

2

 ግቢ ገብርኤል አካባቢ ነዋሪዋ ወጣት መሰረት ምረቴ 10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስዳ መሰናዶ የመግባት ውጤቷን በመጠባበቅ ላይ ነች። ከትምህርቷ ጎን ለጎን በእህቷ ምግብ ቤት ውስጥ ተቀጥራ ትሰራለች። በቀጣይ ዓመት መሰናዶ ትምህርቷን ለማስገባት የሚያስችል ውጤት እንደምታመጣ ተስፋ አላት። መሰናዶ ገብታ በትምህርቷ ልትገፋ ሀሳብ አላት። ከትምህርት ጎን ለጎን የንግድ ሥራዋንም ላለማቋረጥ አስባለች። በቀጣይ ጊዜያት ከተቀጣሪነት በመውጣት የራሷን ምግብ ቤት ለመክፈት እቅድ እንዳላትና በንግዱ ዘርፍ ትልቅ ደረጃ ላይ ለመድረስ እቅዳለች። እቅዷን

 ለማሳካትም አሁን በምትሰራበት የእህቷ ቤት ውስጥ ጠንክራ እየሰራች ደመወዟን እየቆጠበች ነው። ዝግጅትም እያደረገች ነው። ከቁጠባ በተጨማሪ ከመንግሥት መጠነኛ ብድር የመውሰድ እቅድም አላት።

ሰላም ከሌለ ሥራ መስራትም ሆነ ትምህርት መቀጠል አይቻልም የምትለው መሰረት፤ በአዲሱ ዓመት ኢትዮጵያ ሰላምና ፍቅር የሰፈነባት እንድትሆን እንደምትፈልግ ትናገራለች። ሀገሪቷ ሰላም እንድትሆን ሁሉም ሰው ከግጭትና ፀብ ርቆ ለሰላም ዘብ መቆም አለበት ትላለች። ሰዎች እርስ በእርሳቸው ካልተጋጩ ሀገር ሰላም ትሆናለችና። በመሆኑም ከሰው ጋር ላለመጣላትና፣ ጸብን ለማራቅ ዝግጁ መሆኗን ትናገራለች።

አዲስ ዘመን   መስከረም 1 /2012

 መላኩ ኤሮሴ