ወጣቶች ስለ አዲሱ ዓመት ምን ይናገራሉ?

5

ነዋሪነቱ ሽሮ ሜዳ አካባቢ የሆነው ወጣት ደረጀ ደመቀ የፓርኪንግ ሥራ ይሰራል። አዲሱን ዓመት በደስታ ለመቀበል ተዘጋጅቷል። ቤቱን ቀለም እያስቀባ ነው። ለበዓል አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ገዝቷል። ዶሮና ሽንኩርት ገዝቶ ካዘጋጃቸው መካከል ተጠቃሽ ናቸው። በአዲስ ዓመት የራሱን ሕይወት ለመለወጥና በሀገራዊ ለውጡ የበኩሉን ለማበርከት የተለያዩ እቅዶችን አቅዷል። ኢትዮጵያ የተረጋጋ ሰላም እንዲኖራት ምኞት አለው። አዲሱ ዓመት ለመላው ኢትዮጵያውያን የደስታና የብልጽግና እንዲሆንም ምኞት አለው።

በአዲሱ ዓመት ራሱን ለመለወጥም የሚያስችሉ ተግባራትን ለማከናወን ውጥን አለው። ከእቅዶቹ መካከል ቀን ቀን የፓርኪንግ ሥራውን እየሰራ ያቋረጠውን ትምህርት በማታ ለመቀጠል አስቧል። ራሱን ከጸብና ለጸብ ከሚጋብዙ ተግባራት በመቆጠብ ሌሎች ሰዎችም ተመሳሳይ እሳቤ እንዲኖራቸው በመምከር ለሀገራቸው የችግር ሳይሆን የመፍትሄ አካል እንዲሆኑ ለማገዝ አቅዷል።

አዲስ ዘመን   መስከረም 1 /2012

 መላኩ ኤሮሴ