መቋጫ ያልተበጀለት እስራኤል እጣ ፈንታ

18

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የስልጣን ቆይታ በመጨረሻ ያከተመ ይመስላል፡፡ በተካሄደው ምርጫ ለማሸነፍ ይሆናል ያሉትን ሁሉንም ማታለያዎች ሞክረው የነበረ ቢሆንም መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችል በቂ መቀመጫዎች ፓርቲያቸው ማግኘት አልቻለም::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአገሪቱ ነዋሪዎች የተሳሳቱ መረጃዎችን በመስጠት፣ ተፎካካሪዎቻቸው ላይ በማሾፍ ፣ የምርጫ ህጎችን በማፍረስ ፣ በእስራኤል የሚገኙት አናሳ ፍልስጤማውያን ግጭት ውስጥ እንዲገቡ በማድረግ፣ በጎረቤት አገራት ላይ የቦንብ ጥቃት እንዲፈፀም በማድረግ እና በዌስት ባንክ ህገወጥ ሰፈራ በማካሄድ አንድ ሶስተኛው በእስራኤል እንዲያዝ ማድረጋቸው ይጠቀሳል፡፡ በአካባቢው እንደ አሜሪካ እና ሩሲያ መሪዎች እንደ አንድ ልዕለ-ሀይል አገር መሪ ለመሆን ጥረት አድርገዋል።

ኔታናያሁ በስልጣን ዘመናቸው የሙስና ፣ የማጭበርበር እና የማታለል ክሶችን ማስተባበል አልቻሉም ነበር፡፡ የእስራኤልን የወደፊት ሕይወት ማዳን የምችለው እኔ ብቻ ነኝ ብለው በማሰባቸው ለሚሰነዘርባቸው ትችትም ሆነ ማስተካከያ ጆሮ አልሰጡም ነበር፡፡ የተካሄዱት ምርጫዎች ህዝቡ ከኔትንያሁ መንግስት ለመላቀቅ እንደ ህዝበ ውሰኔ የተወሰደ ከሆነ የስልጣን ዘመናቸው አክትሟል ማለት ሲሆን ተመልሰው የመምጣት እድል ላይኖራቸው ይችላል፡፡

ኔታንያሁ እና ሌሎች አማራጮች

አንዳንዶች የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዝቅ አድርገው ይገምታሉ፡፡ ግን እንደዚያ አይደሉም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምንም ነገር ማምለጥ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ሃሳባቸውን በመቀያየርና በመንሸራተት ልምድ ያላቸው ገዥ ናቸው ብለውም ያስባሉ፡፡ የሚቀጥለውን ካቢኔ የማቋቋም ስልጣን ያገኛል ተብሎ ተስፋ ከተጣለበትና 55 የፓርላማ አባላት ወንበር ካለው የአክራሪና ፋሽስት አጋር ጋር የተጣመሩ ሲሆን የቀጣይ ካቢኔ ድልድል ላይ እድል ሊኖራቸው እንደሚችል ይገመታል፡፡

ኔታንያሁ ስልጣን ማግኘት ካልቻሉ አገራዊ ቀውስ ሊመጣ ይችላል፡፡ አለበለዚያ ደግሞ ወደ ጦርነት በመሄድ የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር አቪግዶር ሊቤማን ቀይ መስመሩን ዘለው ወደ ህብረቱ እንዲቀላቀሉ የሚያስገድድ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል፡፡ ከእንደዚህ አይነቱ ምናባዊ ሁኔታዎች አጭር በመሆናቸው ምንም የሚጨምሩት ነገር አይኖርም፡፡ ምክንቱም ኔታንያሁ መንግሥት ለመመስረት የሚያስፈልጓቸው 61 መቀመጫዎችን አላገኙም፡፡

እናም ከመስከረም ወር ይልቅ የሚያዚያ ወር እድለቢስ ሆኖ ሲገኝ በፓርቲው ውስጥ ያሉ ድምፆች ኔታንያሁን ስልጣን እንዳይቀጥሉ አድርጓቸዋል፡፡ ነገር ግን በህጋዊ መንገድ ስልጣናቸው እስኪጠናቀቅ ተስፋ አይቆርጡም፡፡

በጣም የከፋ ነገር ለኔታንያሁ እንደቀድሞው እንደ ኤሁድ ኦልሜርት እስር ቤት ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም እስራኤል መሪዎቻቸውን በጦር ወንጀሎች የመቅጣት እድሉ ከፍተኛ በመሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን አገሪቱ ከነፃነት በፊት እውቅናን መስጠት የተለመደው ነገር ቢሆንም በተቃራኒ ኔታንያሁ የሚመሩት መንግስት ሰላም ከማስፈን ውጪ አማራጭ የለውም፡ ፡

ጠባብ ጥምረት መንግስታት መመስረት ስላልቻሉ ሁለቱ ዋና ዋና ፓርቲዎች – ነጭ እና ሰማያዊ እና ሊክዊድ ለወደፊቱ የብሔራዊ (የአይሁድ) የአንድነት መንግስት ላይ ምናልባትም እንደ ሊበርማን የኢያኤል ቤይንግ ካሉ ሌሎች የቀኝ-ወገን ፓርቲዎች ጋር ድርድር ሊገቡ ይችላሉ፡፡ ምንም እንኳን ይህ ዕድል ቢኖርም በአንድ ዓመት ውስጥ ሶስተኛ ምርጫን ለማካሄድ ምንም ፍላጎት የለም፤ በተለይም ለኔታንያሁ ፡፡

ነገር ግን የመሃል እና በቀኝ የሚገኙ ፓርቲዎች አጠቃላይ መሪነት የሚመሰርቱት ብሔራዊ መንግስት ለወደፊቱ ለእስራኤልም ሆነ የፍልስጤም ዕጣ ፈንታ መልካም አይመስልም፡፡ በእርግጥ ውጤቱ በእስራኤል ምርጫ በጣም ለተጎዱት አሁንም የበለጠ መጥፎ ሊሆን ይችላል፡፡ በተጨማሪም የእስራኤላውያን ምርጫ ከማንኛውም የተለየ መሪ በተሻለ የእስራኤል እና ፍልስጤምን የወደፊት ቅርፅ የሚይዙ ሰፋፊ አዝማሚያዎችን እንዳሉ ያሳያል፡፡

ስድስቱ አዝማሚያዎች

በመጀመሪያው በእስራኤል የመጀመሪያዎቹ ሶስት አስርት ዓመታት ውስጥ መንግስቱን የተቆጣጠሩት ጽዮናዊያን የሚባሉት ግራ ዘመሞች አሁንም ቀጣይነት አላቸው፡፡ በተለይም ላራ እና ሜሬዝዝ በቀጣዩ ፓርላማ ውስጥ ከአረብ ዝርዝር እንኳን ያነሱ መቀመጫዎችን በሚያዙ አነስተኛ ማዕከላዊ ቀኝ ጥምረት ውስጥ ተዋህደዋል፡፡ ሌሎች ትናንሽ ፓርቲዎችን ካልተቀላቀሉ በስተቀር ፓርላማ ለመግባት በትንሹ የሚጠየቀው ሶስት ነጥብ 25 በመቶ ላይሆን ይችላል፡፡ የእስራኤል ግራ የጊዮናዊነት ከመሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ጋር ማስታረቅ ሳይችል ቀርቶ ከሆነ ግን ቢያንስ ፓርላማ የመግባት እድሎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡

ሁለተኛ በፓርላማው መቀመጫዎች ውስጥ ከሦስት አራተኛ በላይ የሚይዙ እጅግ በጣም ከባድ ፣ አክራሪ፣ ማእከል እና የሃይማኖት ቀኝ- ፓርቲዎች ናቸው፡፡ በዚህም እስራል ወደ ጎን ልትለጠጥ ትችላለች፡፡ ፖለቲከኛው ኔታንያሁ መሪነቱን ሊያጡ ቢችሉም፣ ርዕዮተ-ዓለም ለውጡ ግን የእስራኤልን የበላይነት እያደገ እንዲመጣ ያደርገዋል፡፡ ኤፍ ደብሊው ዲ ክለርክ በምርጫው አሸንፎ መውጣት አለበት ብሎ የሚያምን ማንኛውም ሰው ጭንቅላቱን መመርመር አለበት፡፡ የእስራኤላውያኑ የአፓርታይድ ስሪት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከነበረው የቅድመ-1994 ነጮች በጣም ባልተለየ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

650 ሺ ህገ-ወጥ ሰፋሪዎች በሚኖሩባቸው የፍልስጤም ግዛቶች ውስጥ አፓርታይድ ስር መስፋፋቱን ቀጥሏል፡ ፡ በሁለት የተለያዩ እና እኩልነት በሌላቸው ስርዓቶች የሚተዳደር አንድ-ግዛት እውነታ የፈጠረውን የሕገ- ወጥ ሰፈሮች እንቅስቃሴ በአጭሩ ሊቀጭ ይችላል፡፡ ምክንያቱም አንዱ ቡድን ለአይሁድ ሌላኛው ደግሞ ለፍልስጤማውያን ማገዛቸው ስለማይቀር ነው።

ሦስተኛ ባሳለፍነው ሳምንት የተካሄደው ምርጫ እስራኤልያውያን እንደ ኔታንያሁ ላሉ አክራሪ ቀኝ- መሪዎች እንደ አማራጭ ለቅኝ ገዥነት እና ለጦርነት ስማቸው ታዋቂ መሆናቸውን በድጋሚ አሳይተዋል፡፡ እንደ ላቦርስ ይትዝሀክ ራቢ፣ ኤሁድ ባራክ፣ የካዲማ አሪኤል ሻሮን እና የቀድሞው የመከላከያ ኃላፊ ቤኒ ጌንትዝ በጥቁር መዝገብ ሰፍረዋል፡፡ በተለይም የደም መፋሰስ ባመጣው መዘዝ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እንዲገደሉ ዘመቻ አካሂደዋል፡፡ ከፍልስጤማውያን ጋር ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሰፈራ ለማሄድ የተወሰነ ፍላጎት አሳይተዋል፡፡ ነገር ግን ኔታንያሁ አሳፋሪ ስራ ሰሩ ከተባለ ጋንትዝ የጭካኔ ስራ ሰርቷል ማለት ነው።

አራተኛ የሃይማኖት ፓርቲዎች ይበልጥ አክራሪ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ በመንግስቱ የመጀመሪያዎቹ ሶስት አስርት ዓመታት ውስጥ የሃይማኖት ፓርቲዎች ዓለማዊ የሠራተኛ ጽዮናውያን ደጋፊዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ላለፉት አራት አስርት ዓመታት ወደ ልኪውድ እና ወደ ጽንፈኛ መብት ተሟጋች እያደጉ ሄደዋል፡፡ ስለሆነም ለመቀላቀል እንኳን አያስቡም፡፡ ዛሬ ሃይማታዊ ፓርቲዎች ከማዕከላዊ ጽዮናዊ ፓርቲዎች ጋር ጥምረት እየመሰረቱ ይገኛሉ።

አምስተኛ ዓለማዊ እና ሃይማኖታዊ ክፍፍል እየሰፋ ይገኛል፡፡ በዓለማዊ እና በሃይማኖታዊ ተቋማት መካከል ያለው ጥላቻ ባለፈው በፈረንጆቹ ሚያዝያ ወር አንድ መንግስት መመስረት ባለመቻሉ ዋነኛው ምክንያት ሆኖ ይጠቀሳል፡፡ ክፍፍሉ በአብዛኛው ባህላዊ ወይም ማህበራዊ ነው፡፡ የማህበራዊ ተቋማት ስራ የኦርቶዶክስ አይሁዶች ከወታደራዊ አገልግሎት ነፃ መሆንን በሚመለከት ጉዳዮችን የሚቆጣጠር ነው፡፡

ሆኖም ፍልስጤማውያንን በማታለል እና በትውልድ አገራቸው እኩል መብትን በመከልከል ላይ አለመግባባት አለ፡፡ በእርግጥ እንደ ዓለማዊ ወይንም አልፎ ተርፎም አምላክ የለሽ ጽዮናውያን በሰንበት ማሽከርከር እና የተከለከሉ ምግቦች መመገብን የሚቀጥሉት እግዚአብሔር ፍልስጤምን ለአይሁድ ህዝብ ቃል ገብቷል ብለው የሚያምኑ ሰዎች ናቸው፡፡

ከላይ የተዘረዘሩት አደገኛ አዝማሚያዎች በምርጫው የተወዳደሩ ፓርቲዎች ላይ የሚታይ ነው:: ወደ ስድስተኛው አዝማሚያ ብናይ በእስራኤል የፍልስጤማውያን አናሳ እድገት እና ጥምረት ላይ ጥላውን ያጠላው ዘረኝነት ነው። በአንድ ወቅት ትንሽ ተከፋፍለው የመሰረቱት ቡድን ፍልስጤማውያንን በሙሉ እንዳይወከሉ እና በእስራኤል ውስጥ ሙሉ ዴሞክራሲያዊ እና ባህላዊ መብቶችን የሚጥስ አመፅ እንዲነሳ አድርጓል፡፡ ከእስራኤል መብት የሚመነጨው ጥላቻ እና ዘረኝነት ቢኖርም ፍልስጤማውያንን አጥብቀው ይጠላሉ::

የብሔራዊ አንድነት መንግሥት መመስረት የአረብ ቁጥርን በመቀነስ በፓርላማ ውስጥ ሦስተኛው ትልቁ ቡድን መሆን ይፈልጋል፡፡ በተጨማሪም የተቃዋሚ ፓርቲ አመራርን የከፍተኛ ደረጃ የደህንነት መግለጫዎችን ጨምሮ ልዩ መብቶችን ይሰጣል፡፡ ነገር ግን የሚቀጥለው ጠቅላይ ሚኒስትር በፍልስጤማውያን ላይ ዘረኝነት ይበልጥ እያሰፋ ሲሄድ ለተቃዋሚዎቹ የሚሰጠውን መብት ሊያስቀር ይችላል ፡፡

ቀጣዩ ነገር ምንድነው?

እነዚህ ሁሉ አዝማሚያዎች የሚቀጥለውን ጠቅላይ ሚኒስትር ባህሪን መቅረጽ እና ማሰናከላቸውን ይቀጥላሉ፡፡ እንደ ሊክዊድ ያሉ ሁሉም ዓይነት ባህሪ ያለው ፓርቲ በማይገኙበት ጊዜ ወደ ሰላም ከመምጣት ይልቅ ማንኛውንም ከባድ እርምጃ በመውሰድ የብሔራዊ (የአይሁድ) አንድነት መንግሥት መሪ እንዲመጣ ፈቃደኛ አይሆኑም፡፡

በእ.አ.አ 1980 ዎቹ የሰራተኛ ሊክዊድ ብሔራዊ አንድነት መንግስት በመንግስቱ ላይ የተከሰተውን አሰቃቂ መጥፎ ዓመታት ተከትሎ ያመጣቸው እቅዶች አጠቃላይ ከሸፉ፡፡ ለዚህ ደግሞ የመንግስት አስተዳደሩን በድጋሚ በመከለስ ሀያልነቱን አረጋግጧል፡፡ ማንኛውም አዲስ መሪ የእስራኤልን እጅግ ጠንካራ ደጋፊ ካሳየው ከትራምፕ አስተዳደር ጋር የእስራኤል ግንኙነት ለማቆየት እና ለማጠንከርም ይጥራል ፡፡

በእርግጥ የሚቀጥለው ጠቅላይ ሚኒስትር የኋይት ሀውስ አስከፊ “ምዕተ-ዓመት” በጣም ተግባራዊ አካሄድ እና ቅንጅቱን ጠብቆ ለማቆየት ደህንነቱ የተጠበቀ መንገድ ሊያገኝ ይችላል፡፡ አሜሪካውያንን ወደ ውስጥ ለማስቀረት፣ አረቦች ከእስራኤል እንዲወጡ እና ፍልስጤማውያንን ዝቅ ለማድረግ የተሻለውን መንገድ ሊፈጥር ይችላል ፡፡

ይህ በእስራኤል እና ፍልስጤም ውስጥ ሰላምን እና ፍትህ ለሚንከባከቡ ሁሉ የሚያሳዝን ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ቢያንስ በዚህ አመት በተባበሩት መንግስታት የወጡ ሪፖርቶች የሚያሳዩት የኔታንያሁ አምባገነንነትና የፍልስጤማውያንን ስቃይ ነው፡፡ ዘገባው የአልጀዚራ ነው፡፡

አዲስ ዘመን  መስከረም 19/2012

 መርድ ክፍሉ