የደብረብርሀን – አንኮበር የኮንክሪት አስፋልት መንገድ ግንባታ ዛሬ በይፋ ተጀመረ

27

1 ቢልየን ብር የተመደበለት የደብረብርሀን – አንኮበር የኮንክሪት አስፋልት መንገድ ግንባታ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እና  በሚንስትር ማእረግ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዱአለምን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል መስተዳድር አካላት ተገኝተው በአንኮበር  ግንባታውን አስጀምረዋል።

ሰንሻይን ኮንስትራክሽን የተባለ ሀገር በቀል ተቋሯጭ የሚገነባው ይህ መንገድ 42 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን በ2ዓመት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ታቅዶለታል።

በጌትነት ተስፋማርያም