የድንተኛ ህክምና አገልግሎትን ለማጠናከር ከ3ሺህ በላይ የአንቡላንስ ግዥዎች እያከናወነ ነው

22

የኢትዮጵያ የድንተኛ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር 6ኛ አመታዊ ስብሰባ እያካሄደ ነው፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የድንተኛ ህክምና አገልግሎትን ለማጠናከር በ155 ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 755 ጤና ጣቢያዎች የድንገተኛ ህክምና ክፍሎች በቁሳቁስና በሰለጠነ ባለሙያዎች ለማደራጀት ከፍተኛ በጀት መድቦ እየሰራ ነው ብለዋል በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሜዲካል ሰርቪስ ጀነራል ዳይሬክተር ዶ/ር ዳንኤል ገብረሚካኤል፡፡

የአምቡላንሶች ግዥ ተጠናቆ አገልግሎት ሲጀምሩ በአለም ጤና ድርጅት መሠረት አንድ አምቡላንስ ለ25 ሺህ ህብረተሰብ የሚለው መስፈርት ኢትዮጵያ ታሟላለች ብለዋል፡፡ ከጤና ጣቢያዎች በተጨማሪም በመላው አገሪቱ በሚገኙ 6ዐ ሆስፒታሎች የድንገተኛ ህክምና አገልግሎትን ለማጠናከር ከቁሳቁስ ጀምሮ ባለሙያዎችን ለማስልጠን ጤና ጥበቃ በትኩረት እየሰራ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የድንገተኛ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር ኘሬዝዳንት ኘሮፌሰር አክሊሉ አዛዥ ማህበሩ ከተመሰረተ ጀምሮ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጎን በመሆን ባለሙያዎች ለሥልጠና በመደገፍ የነበረው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት እንዲስፋፋ ማህበሩ እየሰራ ነው ተብሏል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በመድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደገው ሻለቃ አትሌት ሐይሌ ገብረሥላሴ የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ልክ እንደ አትሌቲክስ ስፖርት ጽናት ይጠይቃል ብሏል፡፡

አትሌት ሐይሌ በህይወት ማዳን ውስጥ የጊዜ አስፈላጊነት ትኩረት ሰጥቶ ከራሱ ተሞክሮ በመነሳት አብራርቷል፡፡ ለሁለት ቀናት በሚቆየው 6ኛው የማህበሩ ስብሰባ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡