በላይቤሪያ ዜግነት ለማግኘት የሚደረገው ትግል

24

አዲስ የተቋቋመውን የላይቤሪያ መንግስት እየመሩ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ጆርጅ ማኔህ ዊሀ  የራሳቸውን መንግስት ከመሰረቱ አንድ ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ በአገሪቱ የሁለትዮሽ ዜግነት እንዲፀድቅ እና በህገ-መንግስቱ የጥቁሮች መብት ለማስከበር  እንዲሁም በአገሪቱ የሚኖሩ ጥቁር ያልሆኑ ዜጎች እዛው በመወለዳቸው ዜግነት ሊሰጣቸው በሚሉ አጀንዳዎች ተወጥራለች፡፡ ምንም እንኳን የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን የአሜሪካ እና የካሪቢያንን ኢኮኖሚያዊ አገዛዝ ምክንያት በማድረግ የላይቤሪያን ሰፋሪዎች ቅሬታዎች ቢቀበሉም የጥቁሮች ንቅናቄ መደገፍ እና የሁለትዮሽ ዜግነት ጥያቄ መከልከል የሀገሪቱ የ 21 ኛው መቶ ክፍለዘመን የኋላ ታሪክ ምክንያት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር አረጋግጠዋል:: 

ሆኖም ግን ነጻነት  ማግኘት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው ስለሆነ ላይቤሪያውያን በአጠቃላይ እና በሁለት ዜግነት ላይ  በምዕራብ አፍሪካ፣ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ ከ 200 በላይ ሰዎች ቃለ-መጠይቆች ተደርጎ እንደመለሱት ሁለተኛ ዜግነት የሚከለክለው ህግ አለመቀየሩን ጠቅሰዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በቀላሉ ሊቀይሩት አይችሉም:: የላይቤሪያ ዜግነት ትርጉም በማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊ አቋም፣ በጾታ እና በጎሳነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በሁለት ዜግነት እና የጥቁር መብት ለመቀበል ወይም ላለመቀበል ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡

እአአ 2015 ላይ ህገ መንግስቱን የመከለስ ስራ ሲሰራ ነዋሪው ሁለት ዜግነት እና የጥቁሮች መብት ላይ ብቻ ያተኮረው ህግ እንዲቀየር ድምፅ ሰጥተው ነበር፡፡ እአአ 2018 ላይ በተደረገው ጥናት ደግሞ ሁለት ሶስተኛው ነዋሪ ዜግነትን ሲቃወም የጥቁሮች መብት ላይ የሚያተኩረው አሰራር ገደብ ሊበጅለት እንደሚገባም ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡ በተጨማሪም የአገሪቱ ዜጋ መባል ያለበት ጥቁር ህዝብ ብቻ በመሆኑ አገሪቱን መቆጣጠር አለበት ይላሉ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በውስጥ እና በውጭ አገር ያሉ አንዳንድ ላይቤራዊያን ተቀናቃኞች ተቃውሞ ከፍ እያለ የመጣ ሲሆን በሁለት ዜግነት ላይ ያለው አቋም በብሔራዊ ጥቅም ላይ ሳይሆን እራሱን በሚጠቅም መንገድ አስቦት ነው ይላሉ፡፡ ብዙዎቹ እአአ በ 1990 ዎቹ ውስጥ ለፓሪስ ሴንት ጀርሜን ሲጫወት  የፈረንሳይ ዜግነት እንዳልነበረው ጠቅሰዋል፡፡  አንዳንዶች ተቃውሞዎች ደግሞ የጃማይካዊና የአሜሪካ ዜግነት ያላት ሚስቱን  የላይቤሪያ ዜግነት እንድታገኝ ስለሚፈልግ ነው ብለው ክስ ያቀርባሉ፡፡ የተቀሩት ደግሞ  የላይቤሪያን የንግድ ልውውጥ ለማሳደግ ጥቁር ያልሆኑ ዜጎች መሬት እንዲያገኙ አላማ ያደረገ መሆኑን ይናራሉ፡፡ ይህ ሁኔታ የሁለት ዜግነት ተቃዋሚዎችና የጥቁር ተጠቃሚነት ደጋፊዎች መካከል ያለው ፍጥጫ እንዲከር አድርጎታል፡፡ ከፕሬዝዳንት ዊሃ በተቃራኒው የላይቤሪያ የዜግነት አቀንቃኞች አላስፈላጊ እና ዘረኛ ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት በተደረገ ጥናት እና ባሁኑ ጊዜ ምርምር ላይ ተመርኩዞ የሚቀርቡ ማሻሻያዎችን መሰረት ያደረገ አራት ተቃራኒ ምክንያቶች  በፖሊሲ ለመፍታት ጥረት መደረግ አለበት፡፡

እንደ ብሮንበን ማንባይ አይነት ምሁራን እንደሚናገሩት፤ በአብዛኛው የአፍሪካ አህጉራት ዜግነታቸውን ለማስጠበቅ የሚታገሉትና የራሳችን ነው የሚል አመለካከት ያመጡት በቅኝ ገዥ ዘመን ከተለያዩ የእስያ አራት በስደት የመጡ ዜጎች በመብዛታቸው ነው፡፡ በተለይ በአይቮሪኮስት፣ በኮንጎ፣ ኬንያ፣ ሴራሊዮን፣ ዩጋንዳና ዚንባቡዌ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ሴራሊዮን ነፃነቷን ካገኘች በኋላ በሕገ-መንግሥቱ ውስጥ የጥቁር መብት አስገብታ ነበር:: እንደ ቻድ፣ ማላዊ እና ማሊ ያሉ ሌሎች አገሮች ደግሞ በአንድ ወቅ የአፍሪካውያንን ዜጎች የዜግነት መብትን ደንግገዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በአብዛኛው የአፍሪካ ሀገሮች የሁለትዮሽ ዜጎች ሲሆኑ ሌሎቹ እንደ ላይቤሪያ ያሉ ነዋሪዎች ግን ተቃውሟቸውን ቀጥለዋል፡፡

ምንም እንኳን ላይቤሪያ በመሠረቱ አውሮፓ በቅኝ ባትገዛም ከተለያዩ አገራት የተሰባሰቡ ጥቁር ስደተኞች  ኖረውባታል፡፡ ስደተኞቹ በላይቤሪያ የዜግነት መብት የፈጠሩ ቢሆንም መጀመሪያ በላይቤሪያ ይኖሩ የነበሩትን ሰዎች ዜግነት ከልክለው ነበር፡፡ ይህ ሁኔታ በአሁን ወቅት ያለውን ነዋሪ ስለዜግነት ያለውን አመለካከት ቀይሮበታል፡፡ ከዚህ በፊት በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን ሰፋሪዎች  እና  በላይቤሪያ ረዥም ጊዜያት የቆዩ ነዋሪዎች መካከል የነበረው መከፋፈል  በ21ኛው ክፍለ ዘመን ተመላሾችና አሁን ያሉት ነዋሪዎች መካከል የዜግነት ይገባኛል ክርክር እያደረጉ ቢሆንም በአገሪቱ ተከስቶ በነበረው ጦርነት ያልተሰደዱ ዜጎች ግን በዜግነት ይገባኛል ጉዳይ ውስጥ አልተካተቱም፡፡ በመካከለኛው ምስራቅ እና በእስያ የሚገኙ ነጋዴዎች  ለብዙ አሥርተ ዓመታት በላይቤሪያ ውስጥ ኖረዋል፡፡ በዚህም የመሬት ባለቤትነት፣ የመምረጥ  መብት ወይም የህዝባዊ ሥልጣን መያዝ  ላይ የላይቤሪያ ዜጎች ላይ ውድድር ፈጥረውባቸዋል፡፡

በላይቤሪያ ውስጥ የመሬት ይዞታ በዋናነት በዜጎች የተያዘ ቢሆንም በዊሀ አገዛዝ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለውጭ ኢንቨስትመንት በመስጠት የፓልም ዘይት ምርትና ለሌሎች አግሮ ኢንዱስትሪዎች ውሏል፡፡ ይህ የመሬት አጠቃቀም ነዋሪውን ሳይጎዳ መሆን ሲገባው በዛ መንገድ  ባለመከናወኑ ህዝባዊ ሰልፍ አስከትሏል፡፡ በላይቤሪያ በነበሩት ግጭቶች ምክንያት ነዋሪዎች ያልተማከለ የመሬት አጠቃቀም ነበረው፡፡ ጦርነቱ  ካበቃ በኋላ ከውጭ የነበሩት ዲያስፖራዎች አንዳንዶቹ የዜግነት መብታቸውን ለማግኘት ጥረት ሲያደርጉ ተነፍገዋል፡፡ እናም ቀድሞ በአገሪቱ ያፈራው ንብረቱን ሁሉ እንዲተዉት በመደረጉ  ግጭቶች ተፈጥረዋል፡፡ በላይቤሪያ እአአ በመስከረም ወር 2018 ታሪካዊ የመሬት ባለቤትነት ህግን ለማፀደቅ ሙከራ ሲደረግ አዲሱ ህግ እንዴት ነዋሪ ላልሆኑ ዜጎች ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌዎችን አክብረው ለሰብአዊ እና ለትምህርታዊ አላማዎች የሚሆን መሬት እንዲኖራቸው ያስቀምጣል፡፡

የላይቤሪያ ዜጐችን ለመጠበቅ የወጡ ደንቦች በተለይም በፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ የሆኑት ግልጽነት የሌለባቸው ናቸው:: በአሁን ወቅት የሁለት ዜግነት ምክንያት አንዳንድ ነዋሪዎች ህግ  በመጣስ ሁለት ፓስፖርት ይዘዋል፡፡  ለምሳሌ  በአሜሪካ የላይቤሪያ ዲፕሎማትና አምባሳደር ገረሊ ቲ ጊብሰን አሜሪካን ፓስፖርት በመያዛቸው ውድቅ ተደርገዋል፡፡ አምባሳደሯ ለሁለት ዜግነት እንዴት እንደያዙ ተጠይቀው አጥጋቢ ምላሽ በመስጠታቸው በእንግሊዝ የላይቤሪያ አምባሳደር ተደርገው ተሹመዋል፡፡ እነዚህ ታሪኮች በአደባባይ  የተወሩና ሁሉም የሚያውቃቸው ቢሆኑም ብዙዎቹ የላይቤሪያ ህጎች  ግዴታና መብቶችን ለይቶ ያስቀመጠ አይደለም፡፡ ጥቁር ያልሆኑ ወይም ሁለት ዜግነት ያላቸው ዜጎች በአገሪቱ ምን አይነት ኃላፊነት እንዳላቸው የለየ ባለመሆኑ ህጎች ሲለዋወጡ ሀብታምና ሀይለኛ የሚያደርገው ሊሆን የሚችልባቸው አዝማሚያዎች አሉ፡፡

ላይቤሪያ በውጭ አገር ካሳተመቻቸው ገንዘቦች በአንድ ኮንቴነር የነበረና 60 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ ያለው ገንዘቧ የገባበት እንደማይታወቅ መገለፁ ይታወሳል። በዚህም ተጠያቂ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ የአገሪቱ ባለስልጣናትና የባንክ ገዥዎች ከአገር እንዳይወጡ እገዳ ተጥሎባቸዋል። የቀድሞ የአገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ሚልተን ዊክስ በሚደረገው ምርመራ ፖሊስን ለመተባበር ዝግጁ እንደሆኑ ነገር ግን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ባለፈው ዓመት ከታተመ በኋላ ጠፋ ስለተባለው የገንዘብ ኮንቴነር የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

“እኔ ራሴ ጠፋ ስለተባለው ገንዘብ፣ እነዚህ ውንጀላዎች ከየት እንደመጡ ማወቅ እፈልጋለሁ” ብለዋል። ቀደም ሲል የአገሪቱ ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር እንዳስታወቀው 60 ሚሊዮን ዶላር ጠፋ ከመባሉ ጋር በተያያዘ ከአገር ውስጥ እንዳይወጡ ከታገዱ 15 ሰዎች መካከል የባንክ ገዥው ይገኙበታል። የማዕከላዊ ባንኩ ምክትል ገዥ የሆኑት የቀድሞ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ ልጅ ቻርልስ ሰርሊፍ ከታገዱት መካከል አንዱ ናቸው። ኤለን ሰርሊፍ እስካሁን ጉዳዩን በሚመለከት ያሉት ነገር የለም። መንግሥት ወደ አገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ መግባት ሲኖርበት በዚያው ጠፋ የተባለው ገንዘብን በሚመለከት ከፍተኛ ምርመራ እንደሚያደርግ ያስታወቀ ሲሆን ነገሩ የአገርን ደህንነት አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችልም አመልክቷል የላይቤሪያ ዴይሊ ኦብዘርቨር ማዕከላዊ ባንክ የጠፋ ገንዘብ የለም በማለት ነገሩን እንደካደ ተዘግቧል።

ፕሬዝዳንት ዊሃ በፈረንጆቹ አዲስ አመት ጥር 2019 እንደተናገሩት፤ አገሪቱ ባዶ ካዝና በመያዟ ኢኮኖሚው ወድቋል፡፡ ነገር ግን እሱ ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ በ12 ወራት ውስጥ በተሰሩ ስራዎች ማህበራዊ ኢኮኖሚው ማንሰራራት  ጀምሯል፡፡  ፕሬዚዳንቱ የድሃውን ህይወት ለመቀየር አጀንዳ መቅረፃቸውን ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ግን በአገሪቷ ውስጥ የማታለያ ቤቶችን ለመገንባት የህዝብ ገንዘቦችን  አባክነዋል ተብሎ ተወንጅለዋል፡፡ በዚሁ ጊዜ ውስጥ የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ነበር፡፡ 100 ሚሊዮን ዶላር ከላይቤሪያ ወደብ ተወስዶ የት እንደገባ አልታወቀም፡፡ በአጠቃላይ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የብድር ስምምነቶች የሀገሪቱን ዕዳ እንዲቀንስ አድርገዋል፡፡

 

አዲስ ዘመን ጥር 27/2011

በመርድ ክፍሉ