በአሳንሰር ውስጥ ለሦስት ቀናት

18

ረጃጅም ህንፃዎች ከሚሠራላቸው ደረጃ በተጨማሪ የሚገነቡ አሳንሰሮች በተለይ ለዓቅመ ደካሞች፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለነፍሰ ጡሮችና በፍጥነት ወደ ህንፃዎቹ ወጥተው ጉዳያቸውን እንዲያስፈፅሙ ክፍተኛ እገዛ ይሰጣል። እነዚህ አሳንስሮች በአማራጭነት እገዛ የመስጠታችውን ይህን ያህል አንዳንድ ጊዜ በሚገጥማቸው ብልሸት ግለሰቦችን ከጉዳዮች ሲያስተጓጉሉም ይስተዋላል።

\
ሰሞኑን በምጣኔ ሀብትና በቴክኖሎጂ በበለፀገችው አሜሪካ ኒውየርክ ከተማ አሳንሰር ተዘግቶባቸው ለስስት ቀናት ስለቆዩ ወይዘሮ አስንብቧል።በኒውየርክ መዲና ውስጥ በሚገኝ በአንድ ባለፀጋ መኖሪያ የተፈፀመው ይህ ክስተት የህንፃው ባለቤት ቢሊዮነርና የባንክ ኢንቨስትመንት ዋረን ስቴፈንሰን እና ቤተሰቦቻቸው ለጉዞ ርቀው ወጥተው በነበረበት ወቅት የተፈጠረ ነው ። ማሪተስ ፎርታሊዛ የተባሉት በዕድሜ ጠና ያሉት አረጋዊት በባለሀብቱ ዋረን ስቴፈን መኖሪያ በቤት ሠራተኝነት የሚያገለግሉ ናቸው።

ቢቢሲ እንደዘገበው በቤቱ ሁለተኛና ሦስተኛ ወለል መካከል አሳንሰሩ ወይም ሊፍቱ ተበላሽቶ በመቆሙ ያለ እህል ውሃ ሦስት ቀን ለመዋልና ለማደር ተገደዋለ። በመጨረሻው በአንድ የቤተሰቡ አባል እርዳታ ነፍሳቸውን መታዳግ ችለዋል። ሴትየዋ ኃይለኛ ድርቀት ያጋጠማቸው ቢሆንም ወደ ሆስፒታል ከተወሰዱ በኋላ የጤንነት ሁኔታቸው መሻሻል አሳይቷል።

ባለሀብቱ በጉዳዩ ዙሪያ በባንካቸው በኩል ባወጡት መግለጫ “ጉዳዩ ባልታሰበ ሁኔታ የተከሰተ አጋጣሚ ነው፤ ምርመራ ተካሂዶ ወደፊት በድጋሚ ተመሳሳይ አደጋዎች ፈፅሞ እንዳያጋጥመን ትክክለኛ ርምጃ እንወስዳለን” ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ጎበዝ እኛም እንደዚህ ዓይነት ክስተት እንዳያጋጥመን መጠንቀቅ ተገቢ ነው። በተለይ ቅዳሜና እሁድ የተወሰነ ሠራተኛ ለሥራ በሚገባባቸው መሥሪያ ቤቶች ብቻችንን ከሆንን በተቻለ መጠን በአሳንሰር ወይም ሊፍት ላለመጠቀም ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው። ወደ ፎቅ ለመውጣት አሳንሰር ገብተን ቢበላሽ የቴክኒክ ባለሙያዎች ወዲያው የሚገኙበትም ዕድል አናሳ ነው ብዙ ሠራተኛም አይኖርም።

አዲስ ዘመን ጥር 28/2011

ኃይለማርያም ወንድሙ