ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በጥር ወር 2011 ዓ.ም ያከናወኗቸው አበይት ተግባራት

27
 • ጥር 1/2011 ዓ.ም

1/ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የአየርላንድ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካርን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ይህ ይፋዊ ጉብኝት በኢትዮጵያና በአየርላንድ መካከል ያለውን ከ20 አመታት በላይ የዘለቀ ግንኙነት የበለጠ ያጠናክራል ተብሎ ታምኖበታል።

 • ጥር 3/2011 ዓ.ም

1/ የመከላከያ መማክርት (ካውንስል) በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ውይይት ባደረጉበት ወቅት ዶ/ር ዐቢይ ተገኝተዋል፡፡

 • ጥር 4/2011 ዓ.ም 1/ የሚኒስትሮች ም/ቤት ባካሄደው 61ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተሳተፉ፡፡ ም/ቤቱ በተለያ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
 • ጥር 5/2011 ዓ.ም

1/ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር በዘርፉ እየተካሄዱ ባሉ የለውጥ ሂደቶች ዙሪያ ተወያዩ።
የዘርፉ ማሻሻያ የፋይናንስ ተቋማቱን አቅም በመገንባት የበለጠ ተፎካካሪና ብቁ ሆነው ምጣኔ ኃብትን ለማሳደግ ያላቸውን ሚና በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር።

 • ጥር 6/2011 ዓ.ም

1/ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማቡዛን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ:: በህዳር ወር ኢትዮጵያን የጎበኙት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፖሳ ጋር የተደረገው ውይይት ቀጣይ የነበረው ይህ ውይይት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነትና ትብብር በማጥናከር ላይ ያተኮረ ነበር::

2/ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲፕሎማቶች ጋር በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ውይይት አደረጉ፡፡ ጠ/ሚሩ እንደ ዲፕሎማት ዓለም አቀፋዊ አዝማሚያዎችን በመረዳት በኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ላይ የተመሰረተ ሀሳብና አሠራር መመስረት አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው ነበር።

 • ጥር 9/2011 ዓ.ም

1/ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሚመክረውና በአፍሪካ ህብረት በተዘጋጀው የመሪዎች ከፍተኛ ጉባኤ ላይ ተሳተፉ፡፡

 • ጥር 10/2011 ዓ.ም

1/ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፣ ለክርስትና እምነት ተከታዮች ‘‘እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ’’ በማለት መልዕክት አስተላለፉ

 • ጥር 12/2011 ዓ.ም

1/ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከልዑካን ቡድናችው ጋር የአውሮፓ ጉብኝታቸውን ጀመሩ:: በዳቮስ ስውዘርላንድ በሚካሄደው የአለም የኢኮኖሚ ጉባኤ መድረክ ላይ ንግግር ከማድረግ ጎን ለጎን በአውሮፓ ጉብኝታቸውም ከተለያዩ የአለም አቀፍ የልማት አጋሮች ጋር ለመወያየት እቅድ ይዘው ነበር፡፡

2/ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ የአውሮፖ ጉብኝታቸው የመጀመሪያ መዳረሻ የሆነችው ታሪካዊቷ ከተማ ሮም ጣሊያን ደረሱ:: በሮም ሲደርሱም የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸው ነበር፡፡

 • ጥር 13/2011 ዓ.ም

1/ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በጣሊያኑ ጠ/ሚር ጁሴፔ ኮንቴ አቀባበል በፓላዞ ቺጊ/ብሄራዊ ቤተ መንግስት ተደረገላቸው:: ሁለቱ መሪዎች ባካሄዱት የሁለትዮሽ ውይይት ወቅትም ከአዲስ አበባ ምፅዋ በሚዘረጋው የባቡር ሃዲድ ዙሪያ ትብብራቸውን አንድ ደረጃ ከፍ ስለማድረግ ተወያይተዋል::

2/ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የጣሊያኑን ፕሬዝዳንት ሰርየጎ ማታሬላን በክዩሪናል ቤተ መንግስት ጎበኙ:: ሁለቱም መሪዎች በአገራቱ መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነትና በቀጣይ የትብብር ቁልፍ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል::

3/ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት መንግስታት የአለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤዝሊ ጋር ተገናኙ:: የአለም የምግብ ድርጅት ኢትዮጵያን በምግብ ደህንነት: በተመጣጠነ ምግብና በአቅም ግንባታ ዘርፎች እንደሚረዳ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ አስታውሰዋል::

4/ ሁለተኛ የልማት አጋር ውይይታቸውን የግብርና ልማት አለም አቀፍ ፈንድ ፕሬዝዳንት ጊልበርት ሆዉንግቦ ጋር አካሂደዋል:: ፕሬዝዳንቱ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ባለፉት ጥቂት ወራት በአገሪቱ የተመዘገቡትን ለውጦች ለማምጣት ያሳዩትን ቆራጥነት አድንቀዋል::

5/ ጣሊያን ሮም የሚያደርጉትን የልማት አጋሮች ውይይት በመቀጠል ከተባበሩት መንግስታት የምግብና የእርሻ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆዜ ግራዚያኖ ድ ሲልቫ ጋር ተወያዩ:: ዋና ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እየተጫወተች ይለውን ሚና በማድነቅ ሰላም ዋነኛ ቅድመ ሁኔታ ነው ብለው ነበር::

6/ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በቫቲካን የሚገኘውን የቅዱስ ስጢፋኖስ የአቢሲኒያ ቤተክርስቲያን ጎበኙ:: በጉብኝቱ ወቅትም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል በጠ/ሚሩ አነሳሽነት የተገነባውን የሰላም ድልድይ ያስታወሱት ካርዲናል አባ ብርሃነ ኢየሱስ አቀባበል አደረጉላቸው፡፡

7/ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የሮም ጉብኝታቸው ማጠናቀቂያ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያንና የቫቲካን ራስ አገዝ ከተማ መሪ ቅዱስነታቸው አቡነ ፍራንሲስን አነጋገሩ:: በተጨማሪም ከቅዱስ ከተማዋ ዋና አስተዳዳሪ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ጋር በኢትዮጵያና በቫቲካን የጋራ ፍላጎቶች ላይ አተኩረዋል::

 • ጥር 14/2011 ዓ.ም

1/ በሲውዘርላንድ ዳቮስ በተካሄደው የ2019 የአለም የኢኮኖሚ ጉባኤ ይፋዊ የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ ተሳተፉ 2/ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በአለም የኢኮኖሚ ጉባኤ ጎን ለጎን የዱባይ ኢንቨስትመንት ፈንድ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑትን መሀመድ አል ሼይባንን አነጋገሩ::

3/ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በዳቮስ ከኦፕን ሶሳይቲ ኢኒሼቲቭ ኃላፊ ጆርጅ ሶሮስ ጋር ውይይት አካሄዱ። ሁለቱ ወገኖች በምርጫ፤ በዲሞክራሲያዊ ስርዓት፤ በፍትህ እና በኢኮኖሚያዊ ተሣትፎ እንዲሁም በተቋማዊና እና የቁጥጥር ማሻሻያዎችና ተግደሮቶቻቸው ዙሪያ ሀሳቦችን ተቀያይረዋል።

4/ ከበርካታ አገሮች ከተመረጡ ኩባንያ የስራ ኃላፊዎች ጋር የግል ኢንቨስትመንት መሳብ የሚቻልባችው ዕድሎችን ለመለየት የሚያስችል የኢንቨስትመንት ስትራቴጂክ ውይይት አካሄዱ።

 • ጥር 15/2011 ዓ.ም

1/ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በ ዳቮስ: ሲውዘርላንድ የነበራቸውን የአውሮፓ ቆይታ በተሳካ ሁኔታ አጠናቀዉ ወደ ብራስልስ: ቤልጅየም አቅንተዋል::

2/ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ተባባሪ ሊቀመንበር ከሆኑት ቢል ጌትስ ጋር ተገናኝተው ተወያዩ::ጠ/ሚሩ ፋውንዴሽኑ በኢትዮጵያ በጤና: ግብርና: እንዲሁም አቅም ግንባታ ዘርፎች ለሚያደርገው ድጋፍ አመስግነዋል::

3/ ከአሊባባ ሊቀመንበር ጃክ ማ ጋር ተገናኝተው ገንቢ ውይይት አድርገዋል። ሁለቱ ወገኖች ምጡቅ የቴክኖሎጂ እድገት በገበያ እና ማህበረሰብ ላይ የሚያመጡትን ለውጥ በተመለከተ ተወያይተዋል።

4/ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በአለም የኢኮኖሚ ጉባኤ ላይ ንግግር አደረጉ፡፡

5/ ጠሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአለም የኢኮኖሚ ጉባኤ ጎን ለጎን ከቤልጅየሙ ጠ/ሚር ቻርልስ ማይክል ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አከሂደዋል።

6/ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የአለም የኢኮኖሚ ጉባኤ መስራችና ሊቀመንበር ከሆኑት ከፕሮፌሰር ክላውስ ሻዋብ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዱ። ጠ/ሚሩና ፕሮፌሰር ሻውብ ቁልፍ የሆኑ ዓለም አቀፍ ፈተናዎችን ለመፍታት በንግድ፣ በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ፣ በሲቪል ማህበረሰብ ውስጥ የተቀናጀ አሠራርን አስፈላጊነትን ተወያይተዋል።

7/ ጠ/ ሚር ዐቢይ አሕመድ የአለም ባንክ ተጠባባቂ ፕሬዝደንት የሆኑትን ክርስታሊና ጂኦርጂቫን አነጋገሩ። ጠሚ/ሩ የአለም ባንክን ዝርፈ ብዙና ጠንካራ የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ በማድነቅ ድጋፉ እንዲቀጥል ጠየቁ።

*ጥር 16/2011 ዓ.ም

1/ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና ልዑካቸው ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት እና የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይና ደህንነት ፖሊሲከፍተኛ ተወካይ ፌዴሪካ ሞግሄርኒ ጋር ስብሰባ አካሄደ፡፡

2/ በብራስልስ የሚያደርጉትን ስብሰባ በመቀጥል ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ጆን-ክላውድ የንከር ጋር ተገናኝተው ተወያዩ:: ሁለቱ ወገኖች ሶስት የፋይናንስ ስምምነቶች ሲፈረምም ተገኝተዋል::

እነዚህም የ 130 ሚሊዮን ዮሮ ስምምነቶች ዘላቂ ሀይል ማመንጨት: አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክና ስራ ፈጠራ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ ይውላል::

3/ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የቤልጂየም የስራ ጉብኝታቸውን ከአውሮፓ ካውንስል ፕሬዝደንት ዶናልድ ተስክ ጋር በመገናኘት ጀምረዋል። በውይይታቸው ወቅትም በጋራ ጥቅምና የትብብር መስክ ዙሪያ አተኩረዋል።

4/ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተሳካ ሁኔታ የአውሮፓ ጉዟቸዉን አገባደው አጠር ያለ የከተማ ጉብኝት አድርገውም በብራስልስ የሚገኘዉን የኢትዮጵያ ኤምባሲን ጎበኙ::

 • ጥር 17/2011 ዓ.ም

1/ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሀማት ጋር በመጪው የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ዝግጅት ዙሪያ በጠዋት በጽ/ቤታችው ተገናኝተው ተወያዩ፡፡

 • ጥር 18/ 2011 ዓ.ም 1/ ከሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ኡመርና የኢትዮጲያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አህምድ ሽዴ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል::
 • ጥር 19/ 2011 ዓ.ም

1/ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የማስፋፊያ ሥራ በይፋ መረቁ::

2/ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ያደረጉትን ጉብኝት በመቀጠል በአየር መንገዱ አቪየሽን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤትን: የጥገናና ኤሮስፔስ መገጣጠሚያ እንዲሁም የካርጎና ሎጀስቲክስ ማእከላትን ጎብኝተዋል::

3/ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ስካይላይት ባለ አምስት ኮከብ ሆቴልን መርቀው ከፈቱ::

 • ጥር 20/2011 ዓ.ም

1/ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የሚኒስተር መስሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት የ100 ቀናት ዕቅድን የአፈፃፀም ግምገማ መሩ፡፡

2/ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀድሞ አፈ ጉባኤ ዳዊት ዮሃንስ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ሀዘናቸውን ገልጸዋል::

3/ ኢትዮጵያን እየጎበኙ ካሉት ከጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ስታይንማየር ልዑካቸውን ተቀብለው አነጋገሩ።

4/ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በብሄራዊ ቴአትር በየሶስት ወሩ የሚካሄደውን የኪነ ጥበብና የባህል ምሽት ተካፈሉ፡፡

 • ጥር 21/2011 ዓ.ም

1/ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከጥር 20 የቀጠለውን የሚኒስትርና ተጠሪ መስሪያ ቤቶችን የ100 ቀን እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መርተዋል::

 • ጥር 22/2011 ዓ.ም

1/ ለዳያስፖራ ትረስት ፈንድ አስተዋፅኦ ለማበርከት በተሰራው አጭር ቪዲዮ ለተሳተፉ የዘርፉ ባለሙያዎች የተሰማቸውን አድናቆትና ምስጋናቸውን አቀረቡ፡፡

 • ጥር 24/2011 ዓ.ም

1/ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከአባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጡ ጥር 25 ቀን 2011 ዓ.ም 1/ የሚኒስትሮች ም/ቤት ያካሄደውን 62ኛ መደበኛ ስብሰባ መሩ፡፡

ም/ቤቱ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል:: 2/ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያዩ፡፡

*ጥር 26/2011 ዓ.ም

1/ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች የሚገኘውን የጊዳቦ ግድብ ስራ ፕሮጀክት መረቁ: 2/ ከጊዳቦ ግድብ ምርቃት ጎን ለጎን ከኦሮምያ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ጋር በመሆን የጉጂ አባ ገዳና የዞን ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሄዱ::

 • ጥር 27/201 ዓ.ም

1/ የሚኒስትሮች ም/ቤት ጥር 27 ቀን 2011 ያካሄደውን 14ኛ አስቸኳይ ስብሰባ መሩ፡፡

ም/ቤቱ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ጥር 28/2011 ዓ.ም 1/ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለክንፈ የብሔራዊ የደህንነት ጥናት ተቋም ተመራቂዎች ንግግር አደረጉ።

የደህንነት መኮንኖቹ ባለፉት ጥቂት ወራት የብሄራዊ ደህንነትና መረጃ ማእከል፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲና የአገር መከላከያ ሰራዊት የደህንነት አገልግሎት ማሻሻያዎችን ተከትለው ሲሰለጥኑ ነበር።

 • ጥር 29/2011 ዓ.ም

1/ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የድንገቴ ጉብኝታቸውን በመቀጠል በፌዴራል የመካከለኛ ገቢ ግብር ከፋዮች ቢሮ በመጎብኘት ገለጻ ተደርጎላቸዋል። ከቢሮው ሰራተኞች ጋር እንዲሁም የዜግነት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት እየተጠባበቁ ከነበሩ ግብር ከፋዮች ጋር ተገናኝተዋል።

2/ አዲስ አበባ የገቡትን የጊኒ ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴን በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በተደረገ የእንኳን ደህና መጣችሁ ስነስርአት ላይ በመገኘት ተቀበሏቸው።

 • ጥር 30/2011 ዓ.ም

1/ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በጽ/ቤታቸው የጊኒ ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴንና ልዑካቸውን ተቀብለው አነጋገሩ። በአትዮጵያና በጊኒ መካከል ስላለው መልካም ወዳጅነት የጠቀሱት ጠ/ሚሩ ግንኙነቱን ለማጠናከር መልካም መሰረት እንደሚጥልም ጠቀሱ።

2/ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአውሮፓ ህብረት አለም አቀፍ ልማት ትብብር ኮሚሽነር ኒቨን ሚሚካን ጋር ከቀትር በኋላ በጽ/ቤታቸው ተወያዩ። ውይይቱ ጠ/ሚሩ በቤልጅየም ብራስልስ ይፋዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከአውሮፖ ህብረት ኮሚሽን አመራሮች ጋር ካደረጉት ውይይት የቀጠለ ነበር::

በድልነሳ ምንውየለት