«አፍሪካውያን ተንከባካቢ ለሌላቸው ህፃናትና አረጋውያን ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩ ይገባል»ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው

21

አዲስ አበባ፡- (ኤፍ.ቢ.ሲ)፡- አፍሪካውያን ተንከባካቢ ለሌላቸው ህፃናትና አረጋውያን ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩ እንደሚገባ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው ገለጹ።

የአፍሪካ ቀዳማዊት እመቤቶች ጉባኤ ትናንት በአዲስ አበባ በተካሄደበት ወቅት ንግግር ያደረጉት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ ‹‹አፍሪካውያን ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች ትኩረት በመስጠት ሊሠሩ ይገባል›› ብለዋል።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ እንደገለጹት፤ በአፍሪካ በአሁኑ ወቅት በየአካባቢው ረዳት ያጡ ህፃናትና አረጋውያን አሉ፡፡ የእነዚህን ችግር ለመፍታት የእናትነት ፍቅር በመስጠት ሊደረስ ላቸው ይገባል። ዓመቱም የፍቅርና የመስጠት ዓመት ሆኖ እንዲጠናቀቅም ተመኝተዋል።

አሁን ላይም በኢትዮጵያ ለአካል ጉዳተኞች፣ ረዳት ለሌላቸው አረጋውያንና ህፃናት የተለያየ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ቀዳማዊት እመቤቷ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ 22 ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት መታቀዱን ጠቁመው፤ እስካሁን የ15ቱ ግንባታ መጀመሩንም ገልፀዋል፡፡

የቀዳማዊት እመቤቶች ጉባኤ የተካሄደው ‹‹አፍሪካን ለመለወጥ በተለይ ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች ትኩረት መስጠት›› በሚል መሪ ሐሳብ ነው።

አዲስ ዘመን የካቲት 5/2011