የታላቁ ህዳሴ ግድብን ወቅታዊ አቋም የሚቃኝ ግምገማ ተደረገ

65

አዲስ አበባ፡- የታላቁ ህዳሴ ግድብን ወቅታዊ አቋም የሚቃኝ ግምገማ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ተደረገ፡፡ ግምገማው የተካሄደው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት ነው፡፡

 የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ትናንት በድረገጹ እንዳስነበበው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ አሁን ያለበትን ደረጃ በተመለከተም የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ እንዳቀረቡት የሲቪል ምሕንድስና ሥራው ሰማንያ ሦስት በመቶ፣ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራው ሃያ አምስት በመቶ፣ የብረታ ብረት ሥራው አሥራ ሦስት በመቶ በአጠቃላይ ፕሮጀክቱ ክንዋኔ ስልሳ ስድስት በመቶ መሆኑን ገልጸዋል። በፕሮጀክቱ መዘግየት የተነሳም ባጋጠመው የዋጋ ንረት መጀመሪያ ከታቀደው በላይ ከተመደበለት በጀት እስከ አሁን ዘጠና ስምንት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር ፈጅቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በማጠቃለያው ላይ እንደተ ናገሩት፤ በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ ግድ ቡን ማጠናቀቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። በዕለቱም የታላቁ ህዳሴ ግድብን ወቅታዊ አቋም የሚቃኝ ግምገማ በተለያዩ ኮሚቴዎች የቀረበ ሲሆን ግምገማውም፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ አሁን ያለበት ደረጃ፤ የህዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር፤ የአባይ ተፋሰስ ትብብር ማዕቀፍና የግድቡ ሙሌት ደረጃን ያጠቃለለ ነው።

አዲስ ዘመን መጋቢት 22/2011

አብርሃም ተወልደ