የአገሪቱን ፓርላማ ለመበተን ያበቃው የደቡብ ሱዳን ቀውስ

የደቡብ ሱዳን ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን ማንም እርግጠኛ ሆኖ ለመናገር ይቸገራል። ይህቺ አገር በአፍሪካ ረጅም የጦርነት ምድር በመባል ትታወቃለች። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2013 የዲንካ ብሔር የሆኑት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪርና ከኑዌር ብሔር ከሆነው... Read more »

ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለአገር ብልጽግና የድርሻቸውን ለማበርከት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ

ቢሾፍቱ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ከመንግሥት ከግል ድርጅቶች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው ተገለጸ። የኢፌዲሪ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ትናንት በአዳማ ከተማ ባካሄደው... Read more »
Ad Widget

በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን መጠቆሚያ ነጻ የስልክ መስመር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ:- በመጪው አገር አቀፍ ምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ሪፖርት ለማድረግ የሚያስችል ብሔራዊ ነጻ የስልክ መስመር ይፋ ማድረጉን የኢትዮጵያ ሴቶች የሕግ ባለሙያ ማኅበር አስታወቀ ፡፡ የማህበሩ ሥራ አስፈፃሚ ሌንሳ በየነ... Read more »

በቦሌ ክፍለ ከተማ የተገነባው ሁለተኛ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በይፋ ስራ ጀመረ

 ከአስተዳደሩ የፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በቦሌ ክፍለ ከተማ የተገነባውን ሁለተኛው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በይፋ ስራ በማስጀመር ነዋሪዎችን መግበዋል። አንዳችን ለሌሎች... Read more »

“ህወሓት“ እና “ሸኔ“ በሽብርተኝነት መፈረጃቸው ለጸጥታ አስከባሪው ተጨማሪ የሕግ ድጋፍ እንደሚያስገኝለት ተጠቆመ

ሕዝቡን ከቡድኖቹ የሽብር ተግባር እንደሚታደግ ተገለጸ አዲስ አበባ፡- ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ “ህወሓት“ እና “ሸኔ“ በሽብርተኝነት መፈረጃቸው ለጸጥታ አስከባሪው ተጨማሪ የሕግ ድጋፍ እንደሚያስገኝለት ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ፍቃዱ ፀጋዬ አስታወቁ። አቶ... Read more »

ከተማ አስተዳደሩ የአደባባይ አፍጥር መርሐ ግብር መስተጓጎል አስመልክቶ ይቅርታ ጠየቀ

 አዲስ አበባ ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከትናንት በስቲያ ለተፈጠረው የአደባባይ አፍጥር መርሐግብር መስተጓጎል ይቅርታ ጠየቀ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ከትናንት... Read more »

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አለመሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፦ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሰሞኑን የትግራይ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው የሰጡት መግለጫ የግል ሃሳባቸው የተንጸባረቀበት እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ አስታወቀ። የቤተክርስትያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና... Read more »

‹‹በምርጫው መርሐ ግብር ላይ የሚቀርቡ ለውጦች የቴክኒክ፣ የፋይናንስ ፣የፖለቲካና የፀጥታ አደጋን የሚያስከትሉ ናቸው ›› – ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ

አዲስ አበባ ፣ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ መርሐ ግብር ላይ የሚቀርብ የለውጥ ሀሳቦች የቴክኒክ፣ የፋይናንስ ፣የፖለቲካ እና የፀጥታ አደጋን የሚያስከትል እና ከሌሎች ጉዳዮች አንፃር የሚመከርና የሚመረጥ አካሄድ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት... Read more »

እየተባባሰ የመጣው የህንድ የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ

ሁለተኛው ዙር የኮሮና ተሐዋሲው ወረርሽኝ በህንድ ከተቀሰቀሰ ወዲህ በየዕለቱ ከ400 ሺህ ሰዎች በላይ በተሐዋሲው መያዛቸው እየተዘገበ ነው። የሞቱትም ከዚሁ እንደሚበልጡ ከሕንድ የሚወጡ ዜናዎች ያሳያሉ። ቁጥሩም በበሽታው መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጦ ይፋ ከሚወጣው ሊጨምር... Read more »

“የሱዳን መንግሥት የግብፅን ጥቅም ለማስጠበቅ የፕሮፓ ጋንዳ ዘመቻውን ገልብጦት እየሠራ ነው”- ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ አባል

  አዲስ አበባ፡- በሱዳን መንግሥት የራሱን ጥቅም ትቶ የግብፅን ጥቅም ለማስጠበቅ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻውን ገልብጦት እየሠራ መሆኑን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ አባል ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ ገለጹ:: የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ አባል ፕሮፌሰር ይልማ... Read more »