አዲስ አበባ እንገባለን ወደ መቀሌ አናስገባም ፉከራ

ቅኔን በመቀኘት የኔታ (የኔታ) ፍሬውን የሚያህል የለም እየተባለ በሀገራችን በሰፊው ይወራል።እያንዳንዱ ንግግራቸው ቅኔ ነው።የሚናገሩት ቅኔ የረቀቀ በመሆኑ የሚረዳቸው ልቡን በቀናነት የከፈተ ብቻ ነው።የሚናገሩት ጠብ አይልም። ፍጹም ኢትዮጵያዊ ናቸው።ኢትዮጵያን አንስተው አይጠግቡም ።

ይሁን እንጂ የነባሮን ሮማን ፕሮቻዝካ፣ ሞሶሎኒ፣ ክርሲፒ እና ባራቴሪ ፓስታ ቀቃይ እና ደቀ መዝሙር የሆነው አይተ ጭሬ ልድፋው እና ልጁ አይተ እኩይ ግብሩ የየኔታ ፍሬውን ትምህርት መስማቱ አዋጭ እንደሆነ እያወቁ ለመስማት ግን እንደሽንፈት ስለሚቆጥሩት የነሞሶሎኒን ፓስታ ብንቀቅል ይሻለናል ብለው ለጥፋት እጃቸውን በኢትዮጵያ ካነሱ ዓመታት ተቆጠሩ።

የኔታ ፍሬው እነ አይተ ጭሬ ልድፋውን በቅኔ ልክ ልካቸውን ባይነግሯቸው እና ለትዕቢታቸው ማስተንፈሻ መፍትሄ ባይኖራቸው ኖሮ እንዴት ያበግን ነበር።ነገር ግን የኔታ ፍሬው እስከዶቃ ማሰሪያቸው ስለሚነግሯቸው አንጀቴ ይርሳል።አለፍ ሲልም በትረ ሙሴአቸውን ተጠቅመው አይቀጡ ቅጣት ሲቀጡአቸው ሃሴት አደርጋለሁ፡፡

የኔታ ፍሬው እና አይተ ጭሬ ልድፋው ብዙ ጊዜ የሚገናኙት ገበያ መካከል ባለው ድንጋይ ላይ ቆመው ህዝቡን በሚያስተምሩበት ጊዜ ነው።ህዝቡን ሲስተምሩ ድንገት አይተ ጭሬ ልድፋውን እና ልጃቸውን አይተ እኩይ ግብሩ ሲመለከቱ ደማቸው ስለሚፈላ በነገር ይሸነቁጧቸዋል።ህዝቡም የየኔታ ፍሬውን ቅኔ እየሰማ ይደሰታል።የእነ አይተ ጭሬ ልድፋውን የወደፊት እጣ ፋንታ ምን ሊሆን እንደሚችል በቀላሉ ይገምታል።

አንድ ቀን አይተ ጭሬ ልድፋው እና ልጁ የመንደራቸውን ሰዎች ሰብስበው “በሚቀጥለው ዓመት ቀይ ባህርን በመጥለፍ በተንቤን በርሃ ውቂያኖስ እንፈጥራለን። ውቂያኖስ ማዳረስ በማይቻልባቸው የበርሃ አካባቢዎች አቧራን እንደ ውሃ መጠቀም የሚያስችል ቴክኖሎጂን ተጠቅመን በምድረ በዳ ድንጋያማ ቦታዎች ላይ አሳ በማርባት በምስራቅ አፍሪካ እና በዓለም የመጀመሪያው ህዝቦች እንደምንሆን አያጠራጥርም።በዚህም ኢኮኖሚያችንን ወደ ተሻለ ደረጃ ማሳደግ ይቻላል፡፡” ሲሉ ከመካከል አንዱ ተነስቶ እሺ ባህሩን ጠለፍነው ይባል፤ እንዴት ነው ባህር ተጠልፎ ውቂያኖስ ሊሆን የሚችለው? ብሎ ሲጠይቅ አንድ ሌላ አስተዋይ ሰው ከተሰብሳቢዎች መካከል ተነስቶ “ባህር ውቂያኖስ እንደማይሆን ስታውቅ እንዴት ሊፈጠር የታሰበው ውቂያኖስ በእኛ ሰፈር ደም መሆኑ ይጠፋሃል” ሲል አፈጠጠበት።ቀይ ባህር ተስቦ እንገነባዋለን ያሉት ግድብ በሰፈራቸው ህዝብ ደም መሆኑን ነገረው። ጥያቄ ያነሱት ሁለት ሰዎችም ከእነ ልጆቻቸው የቀይ ባህርን ወደ ተንቤን ለመጥለፍ ወደሚደረገው ቁፋሮ ላይመለሱ ተላኩ።

ይህ በእንዲህ እያለ አይተ ጭሬ ልድፋው እና ልጁ “አዲስ አበባን በጥቂት ቀናት ውስጥ ለመያዝ የሚያስችል አቅም ፈጥረናል” ሲሉ ታበዩ።አዲስ አበባን እንደያዙም ባንኮች ፣ ታንኮች ፣ሪልስቴቶችን እና የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለእያንዳንዳችሁ እንደሚሰጡ አባት እና ልጅ ሲነግሯቸው ሁሉም የሞሶሎኒ ፓስታ ቀቃይ ልጅ አጨበጨበ።ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል አንድ የተሻለ ሰው ተገኝቶ ኖሮ “ተስፋየ ካሳ ሞተ አልተባለም ነበር እንዴ?” ሲል አንሾካሸከ።ይህም ሰው የቀይ ባህርን ወደ ተንቤን ለመጥለፍ ወደሚደረገው ቁፋሮ ላይመለስ ተላከ።

ይህን የጭሬ ልድፋውን ድንፋታ የሰሙት የኔታ ፍሬው ህዝብ በተሰበሰበበት በገበያው መካከል ባለው ትልቅ ድንጋይ ላይ ቆመው እንዲህ ሲሉ ተቀኙ “መጋቢ እንበለ ሲሳይ ፣ ጸባቲ እንበለ ማይ (ያለምግብ መጋቢ፣ ያለውሃ ዋናተኛ) እንዴት ሊኖር ይችላል? የማይታሰብ ነው፡፡” የአይተ ጭሬ ልድፋው ድንፋታ እንዲሁ በውጭ የሚኖሩት በዶላር የሰከሩ ፣ በሃጢያት የረከሱ ደጋፊዎቹን እና ለምዕራባውያን አዛዥ ጌቶቹ ለማስደሰት የተመኘው ምኞት እንጂ “ሐለሙ ሕልመ ወአልቦ ዘረከቡ ወይም ህልም አለሙ አንድም ያገኙት የለም አይነት ነው፡፡” ሲሉ ድጋሜ ተቀኙ።ስብከቱን የሰማው ህዝብም የየኔታ ፍሬውን ጉሸማ በደንብ ስለተገነዘበ በጭብጨባ ድጋፉን ገለጸ።

የኔታ ፍሬው ቀጥለውም “እነ አይተ ጭሬ ልድፋው ለእኛ እንደ ዝንጀሮ እና አይጥ ናቸው።ምክንያቱም እነ አይተ ጭሬ ልድፋው እንደ ዝንጀሮ እና አይጥ አጥፊ እና ምቀኛ ናቸው።በመሆኑንም ሌላው ዓለም ዝንጀሮ እና እይጥን የክትባት መለማመጃ ሲያደርጋቸው በእኛ ሀገር ግን ከምቀኝነታቸው እና በህዝብ ላይ ከሚያደርሱት ግፍ ተነስተን ዝንጀሮ እና አይጦችን ለተኩስ መለማመጃ ነው የምናደርጋቸው” ሲሉ የገበያው ሰው በሙሉ በሃሴት አውካካ።

ጥንብ ባለበት አሞራዎች ይሰበሰባሉ እንዲሉ አይጦች እና ዝንጀሮች ባሉበት ቦታ ሁሉ ውሸት ፣ ግድያ፣ ዘረፋ ፣ እርስ በርስ መገዳደል ፣ አስገድዶ መድፈር አይጠፋም።ስለሆነም ሁሉም እዚህ ገበያ የሚገኝ ህዝብ በሙሉ በእነኝህ አይጦች እና ዝንጀሮዎች የጦርነት ልምምድ እንድታደርግ ተጋብዘሃል።ካልሆነ እኩይ ስራቸውን በገበያው ህዝብ ላይ እየፈጸሙ እንዲኖሩ መፍቀድ መሆኑን የኔታ ፍሬው ለህዝባቸው አስረዱ።

ይህን ተከትሎ ህዝቡም ህየንተ አቡውኪ ፣ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ (በአባቶች ፋንታ ልጆች ተተኩልሽ) እንዲሉ የአባቶቹን ገድል ለመድገም ከአልማዝ በጠነከረ አንድነት ተባብሮ ቆመ።የህዝቡ አንድነት አይተ ጭሬ ልድፋውን ከማስደንገጡም ባለፈ የጥፋት አጋሮቹን ብርክ አሲያዛቸው።ተሰብስበውም ተንጫንጩ።የትኛውንም ያህል ተሰብስበው ቢንጫንጩ ግን የየኔታ ፍሬው ሀገር ህዝብ ለማንም ጫጫታ ሸብረክ የማይል ለችግር እጁን የማይሰጥ ህዝብ መሆኑ ታሪክ ህያው ምስክር ነው ።

ሁልጊዜም ቢሆን አይተ ጭሬ ልድፋው ሁለት እድሎችን ለመጠቀም ይጥራ።አንደኛው የማጥፋት ሃይላቸው እንደጠነከረ ሲሰማው በህዝቡ ላይ ጦርነት በመክፈት ህዝቡን ማጎሳቆል ፣ መዝረፍ ፣ መግድል ፣ መድፍርን ነው።በዚህ ጊዜ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላል። ሁለተኛው ድግሞ ህዝቡ ራሱን መከላከል እና ማጥቃት ሲጀምር የሚጠቀመው ስልት ነው።ህዝቡ ማጥቃት ሲጀምር የየኔታ ፍሬው አስተዳደር ሊጠፋው እንደሆነ ገልጾ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲደርስለት እና እንዲያደራድረው ይለምናል።

የአይተ ጭሬ ልድፋውን ሁለት አማራጭ ስመለከት አንድ ነገር አስታወስኩ።በአንድ ወቅት አንድ ሰው ወንዝ እየተሻገረ እያለ ተንሸራቶ ወንዙ ውስጥ ይገባል።ወንዙ ዳር ላይ የዛፍ ስር አግኝቶ ሙጭጭ አድርጎ ይይዛል።ስሩን እንደያዘ ፈጣሪየ ድረስልኝ እያለ አጥብቆ ጮኸ።ፈጣሪውም ጩኸቱን ሰምቶ ይደርስለታል።ፈጣሪውም እየውልህ ጩኸትን ሰምቼ መጥቻለሁ።“እንዳድንህ ትፈልጋለህ? በእኔስ ማዳን ትተማመናለህ? ሲል ይጠይቀዋል።ሰውየውም መዳን እንደሚፈልግ እና በፈጣሪው ማዳንም እንደሚተማመን ለፈጣሪው ይነግረዋል። በዚህ ጊዜ ፈጣሪውም “በኔ የምትተማመን ከሆነ በል በእጅህ የያዝከውን የዛፍ ስር ልቀቀው” ሲል ያዝዘዋል።ሰውየውም “በአንተ አምናለሁ፤ የዛፉን ስር ግን አለቀም” ሲል መለሰ።አይተ ጭሬ ልድፋው እንደዚህ በሁለት ቢላ መብላት የሚፈልግ አይነት ሰው ነው።

አይተ ጭሬ ልድፋው ከሚሰራው እኩይ ስራ የተነሳ አይደለም የታጠቀ ተመልክቶ ይቅር አባባሎችን የያዙ መጽሃፍቶችን ይፈራሉ።የእኩይ ስራ በሚጠነስሱባት ከተማ የጥቅስ መጽሃፍ ብቻ እያዞረ የሚሸጥ ሰው ነበር።አይተ ጭሬ ልድፋው ከመጽሃፍ ሻጩ የጥቅስ መጽሃፍ ገዝቶ ሲመለከት የማህተመ ጋንዲን አባባል ተመለከተ።አባባሉም “ጨካኞች እና ነፍሰ ገዳዮች ለጊዜው የማይደፈሩ መስለው ይታያሉ።ሆኖም በመጨረሻ ሁልጊዜም ይወድቃሉ።አስታውሱ! ሁልጊዜ!!! ‘’ ይላል።

አይተ ጭሬ ልድፋው በጣም ተናዶ እና ጡፎ “ዋይ! ይሄ ለማህተመ ጋንዲ ስለትህነግ መፈጠር እና ከተፈጠረች በኋላ እንዴት ከምድረገፅ እንደምትጠፋ በራዕይ ይታየው ነበር እንዴ? ዋይ! ለዚህ ለማህተመ ጋንዲ እንደትህነግ የውሸት ታሪክ ተፅፎለት እንጅ ትምክህተኛ እና ጠባብ የነበረና የስንት እናቶችን ጡት የቆረጠ ነው።ለፍርድ መቅረብ ነበረበት።ወጣ ወረደ ሁለተኛ የማህተመ ጋንዲ ጥቅስ የያዙ መጽሃፍት በእንደርታ፣ በተምቤን ፣ በአክሱም በአድዋ በአጠቃላይ በትግራይ እንዳይሸጥ።ለሸሁሴን አይደል እንዴ ትንቢት ተናግሮ ለራያ ሜዳ ሊያስጨርሰን ያለው። ደግሞ ማህተመ ጋንዲ ሊጨመር መፍቀድ የለብንም፡፡” ሲል ትዛዝ አስተላለፈ።

አይተጭሬ ልድፋው መጻህፉ እንዳይሸጥ ትዕዛዝ ያስተላልፍ እንጂ የማህተመ ጋንዲን ጥቅስ የያዘውን መጽሀፍ እያነበበ ኖሮ “ለመኖር ብቸኛው አማራጭ ሌላው እንዲኖር መፍቀድ ነው፡፡” የሚል ሌላ አባባል ያያል።በዚህ ጊዜ አይተጭሬ ልድፋው እንደገና ተናዶ “ዋይ! ለዚህ ለማህተመ ጋንዲ ያመዋል እንዴ? እኛ እኮ ሌሎች እንዲኖሩ ከፈቀድን እና ሀገሪቱ ሰላም ከሆነች ለእንደዚህ ለሚያዝናኑን ያሉት “እነአሜሪካ” ገንዘብ አይሰጡንም።በቃ ቅድም ያልኩት ይሁን፤ መጽሃፉ በፍጹም በትግራይ ምድር እንዳይሸጥ!።ሲል ትዕዛዝ ያስተላልፋል።

በአጠቃላይ አይተ ጭሬ ልድፋው እና ጭፍሮቹ ባህሪ ለዝናብ ጌታ ውሃ ነሱት ወይም አባት ላም ይሰጣል ልጅ አጓት ይነሳል አይነት ነው። በቀበሮ ጉድጓድ ሆኖ ለራሱ እየተሰቃየ ሳያልፍለት እንዲኖሩ ያስቻላቸውን መከላከያ ሊያከብሩት እና ሊጠብቁት ሲገባቸው ወጉት።ስንት የሆነችላቸውን ኢትዮጵያንም ለማፍረስ ሲኦል ድረስ እንወርዳለን ሲሉ ተደመጡ፡፡

ይህንን የአይተ ጭሬ ልድፋው ጥጋብ ስመለከት “አይጥ ጠላ ጠምቃ ጠጥታ ጠጥታ፣ ትገለገላለች ድመትን ልትመታ ፡፡” የሚለውን አዝማሪ ፉከራ እና ሽለላ አስታወሰኝ ።

ያም ሆነ ይህ አይተ ጭሬ ልድፋው አቅመ ቢስ ቢሆንም እንኳን ሀገር መበጥበጡን ስላላቆመ ባለመድሃኒቱን በሽተኞች ይፈልጉታል ፣ ጤነኞች አይሹትም እንዲሉ የጥጋቡ ማሻሪያ መድሃኒት ሊሰጠው ይገባል።እርፍ ይዞ ወደ ኋላ የሚያርስ የለም እንደሚባለው ከአሁን በኋላ አይተ ፍሬውን እና ጭፍሮቹን ሳያጠፉ መመለስ አይቻልም።የኔታ ፍሬው ያለውን ህዝብ እና ጦር አስተባብሮ እባብ እንዳይነሳ ጭንቅላቱን እንደሚመታ ሁሉ አይተ ጭሬ ልድፋውን እና ጭፍሮቹን ሁለተኛ ሊነሱ እንዳይችሉ የሚያደርጋቸውን ብልታቸውን ለይቶ መምታት ያስፈልጋል።

ምክንያቱም እሳት እና ውሃ አቀረብኩልህ፤ እጅህን ወደምትሻው ስደድ ፤ የሚጥምህን አንተ ታውቃለህ እንዲሉ አበው ለአይተ ጭሬ ልድፋው ብዙ የሰላም አማራጮች ቀረቡለት። አንዱንም አማራጭ መቀበል አንደ ነውር ቆጠረው።ይባሱኑ የፌዴራል መንግስቱ ስለፈራኝ ነው ብሎ አሰበ።ሀገር አተራመሰ ።ይህን ተከትሎ የፌዴራል መንግስቱ ዱላ ሲያነሳ “ጠዋት የተናገረውን ማታ አያስታውሰውም ” እንዲሉ ባለተጣጣፊ ምላሱ አይተ ጭሬ ልድፋው አዲስ አበባን እቆጣጠራሁ እንዳላለ አሁን ደግሞ መቀሌን ሁለተኛ አላስነካም የሚል የማፈግፈግ ስልት ይዟል።አዲስ አበባን ልትይዙ ትንሽ እንደቀራችሁ ስትነግሩን ሰንብታችሁ በብርሃን ፍጥነት መቀሌን አናስነካም ፉከራ ምን የሚሉት ነው ? የስምንተኛው ሺህ ነገር መቀሌ እና አዲስ አበባ ተጎራባች ከተሞች ሆኑ እንዴ?

በመጨረሻም ሕያዋን ይስአሉ ለሙታን ፣ ሙታን ይስአሉ ለሕያዋን ወይም ያሉት ለሞቱት ይጸልያሉ ፣የሞቱት ያሉትን ያስባሉ። አሁን አይተ ጭሬ ልድፋው እና ግብረ አበሮቹ ያላቸው አማራጭ አንድ እና አንድ ብቻ ነው ።በህይወት ያሉት ለሞቱት መጸለይ ፤ የሞቱትም በትዕቢታቸው የተነሳ መከላከያን ነክተው ሞታቸውን የሚጠባበቁትን እንዲያስቧቸው ማድረግ ነው።ዋይ! ለካ ለእነሱ መስጅድም ሆነ ቤተክርስቲያን መጸለይ አይቻልም።ረክሰዋል።በቃ ለሰይጣን ይስገዱ።

 ሙሉቀን ታደገ

አዲስ ዘመን ጥቅምት 4/2014

Recommended For You