ለፕሮጀክቶች ፕሮፖዛል ጥሪ PISCCA – በፈረንሣይ ኢምባሲ ለኢትዮጵያውያን ሲቪል ማህበራት የተዘጋጅ የልማት ፉንድ «በሴቶች እና በሴት ልጆች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን መከላከል»

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ በሴቶች እና በሴት ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከለ በተዘጋጅዉ ፈንድ የፕሮጀክት ፕሮፖዛል እንዲቀርብለት ጥሪዉን ያቀርባል:: በፈረንሳይ መንግስት በ PISCCA ፈንድ በኩል የገንዘብ ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን በኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ባለቤትነት የሚያዙ ፕሮጀክቶችን የመደገፍን አላማ ይዞ የተዘጋጀ ነው፡፡

* በኢትዮጵያ ውስጥ በሴቶች እና በሴት ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመዋጋት አላማ ያደርገ ፕሮጀክት መሆን ይኖርበታል። በምሆኑም ዋና ዋና ነጥቦችን እንደሚከተለዉ ያካትታል፥

  • የሴት ልጆች ያለእድሜ ጋብቻ
  • የሴቶች ግርዛት
  • የወሲብ ፣ የአካል እና የስነልቦና ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ሴቶች እና ልጃገረዶች እንክብካቤ ማድረግ ፣ አስገድዶ መድፈርን ለጭቆና እና ለግጭት መሳሪያ መጠቀምን ሊያካትት ይችላል
  • የተጎጂዎችን ሕይወት እንደገና መገንባት

* ጥብቅ መረጃ:

  • የፕሮጀክት ትግበራ ጊዜ ፥ ከ 12 እስከ 18 ወር
  • ጂኦግራፊያዊ ሽፋን ፥ ኢትዮጵያ
  • በጀት ፥ ከ 1 እስከ 2.4 ሚሊዮን ብር
  • የሰነድ ማስገቢያ ቀነ ገደብ ፥ እስከ ሚያዚያ 22, 2013 ዓ.ም. 10 ሰዓት ድረስ
  • ኢሜል አድራሻ : frenchgenderfund@gmail.com

ለበለጠ መረጃ እና የማመልከቻ ቅጹን እና ተዛማጅ ሰነዶችን ለማውረድ እባክዎ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ ድህረ ገጽ ይጎብኙ ወይም የሚከተለውን ድር ገጽ ይከተሉ : https://et.ambafrance.org/PISCCA-THE-LOCAL-DEVELOPMENT-FUND-OF-THE-EMBASSY-OF-FRANCE-IN-ETHIOPIA-FOR