Facebook Posts

የኢህአዴግ ውህደት ባለፉት 27 ዓመታት ይስተዋሉ የነበሩ የልዩነትና ጥላቻ ትርክቶችን፣ የብሔር ፅንፈኝነትንና አጋር ድርጅቶችን አግላይ አካሄዶችን የሚፈታ ነው ሲል ሶዴፓ ገለፀ
*****************************************
(ኢፕድ)

ባለፉት 27 አመታት የበላይነት ይዘው የነበሩ የልዩነትና ጥላቻ ትርክቶችን፣ የብሔር ፅንፈኝነትንና አጋር ድርጅቶችን አግላይ አካሄዶችን በሚፈታ መልኩ ኢህአዴግ የጀመራቸውን ለውጦች እንደሚያደንቅ የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ሶዴፓ/ ገለፀ።

ኢህአዴግ ባለፉት አመታት የነበሩትን ስኬቶች ለማስቀጠል፣ የነበሩትን ስህተቶች ለማረምና አዳዲስ እድሎችን ለመፍጠር እንዲሁም አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ እራሱን ለመለወጥና አጋር ድርጅቶችንም ለማቀፍ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ እራስን በራስ ከማስተዳደር ህገ መንግስታዊ ስርዓትና ከምንከተለው የፌዴራል ስርዓት ጋር የማይቃረን፣ አሃዳዊ ስርዓት የመፍጠር ዓላማ የሌለውና ለሀገራችን ወቅታዊ ችግሮች ፍቱን መድኃኒት መሆኑን እንደሚያምን ነው ፓርቲው ያስታወቀው።

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ያወጣው የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት፥ በሶማሌና አፋር ክልሎች አዋሳኝ አከባቢዎች አገራዊውን ለውጥ ለማዳናቀፍ ሌት ተቀን በሚጥሩ አካላት ህቡዕ እንቅስቃሴ የተፈጠረውን ችግር በህገ-መንግስቱ መሰረት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሶዴፓ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

ከሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

በቅድሚያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የኖቤል ሰላም ሽልማት በማግኘታቸው የተሰማውን የላቀ ደስታ ሶዴፓ ይገልፃል።

የሶማሌ ክልል ህዝብ ከሌሎች የሀገራችን ህዝቦች ጋር በመሆን ለዘመናት ለነፃነት፣ እኩልነትና በመፈቃቀድና መከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነት ጠንካራ ትግል ሲያደርግ የቆየ ከመሆኑም ባሻገር እንደ ሌሎች የአገራችን ህዝቦች ሁሉ በገዥ መደቦች ይደርስበት በነበረው በደልና ጭቆና ሳይንበረከክ ክብሩን ያላስደፈረና ለህልዉናው አደጋ የሆኑ ጉዳዮችን ሲመክት የቆየ ሀገር ወዳድ ህዝብ ነው። የሶማሌ ህዝብ በህገ መንግስቱ የተጎናፀፈውን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንዲጠቀምና በሀገር ግንባታ ላይ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ለማስቻል መሪ ድርጅት በማስፈለጉ የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ከ21 ዓመታት በፊት ተመስረቶ የሶማሌ ህዝብን በሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቹ ዙሪያ ሲያታግል ቆይቷል።

ሶዴፓ በሶማሌ ክልል መሪ ፓርቲ ሆኖ በቆየባቸው ባለፉት 21 አመታት ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ሰፋፊ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ድሎችን አስመዝግቧል። ይሁንና ፓርቲው በራሱ የውስጥ ችግር እና በግል ጥቅማቸው የታወሩ የቀድሞ አመራሮች የመንግስትና የህዝብን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው ያደርጓቸው በነበሩት ፀረ- ዴሞክራሲያዊና ፀረ-ፌዴራላዊ ስርዓት አካሄድና ጣልቃ ገብነቶች ምክንያት በሚፈለገው ደረጃ የፖለቲካ ፕሮግራሙን በነፃነት ተግባራዊ ባለማድረጉ ለህዝቡ ቃል በገባው ልክ ኃላፊነቱን መወጣት ያልቻለበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

በሌላ በኩል ሶዴፓ ትክክለኛ አሰራሩን ተከትሎ በህገ-መንግስቱ መሰረት ክልሉ ወደ ዳበረ ዴሞክራሲና ብልጽግና እንዲመራ የሚታገሉ አመራሮችና አባላትም በግል ጥቅም የታወሩ የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች ጥቃትና እንግልት ሲደርስባቸው ቆይቷል። በተጨማሪም የሶማሌ ክልል ህዝብ ህገ-መንግስታዊ የሆነው የፌዴራል ስርዓት በተሟላ መልኩ በተግባር እንዲከበር ባለፉት 27 አመታት ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቢቆይም እንደ ሀገር ለሰላማዊና ዴሞክራሲዊ ትግል ምቹ ሁኔታ ሰላልነበር ጥረቱ የሚፈለገውን ውጤት ሳያመጣ ቆይቷል።

በመሆኑም ባለፉት 27 አመታት በሀገራችን ህገ-መንግስቱና የፌዴራል ስርዓቱ በተገቢው መንገድ ሲተገበር እንዳልነበረ ይልቁንም ሶማሌ ክልልን ጨምሮ የተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች በሞግዚትነት ሲተዳደሩ እንደነበሩ ሶዴፓ ያምናል። እነዚህ የሞግዚት አስተዳዳሪዎች ለግል ጥቅማቸው ማስፈፀሚያ የሚመቻቸውን አካል ለይስሙላ ከማስቀመጥ ባሻገር የክልሉን በጀትና መሬት በመቀራመት የክልሉን ህዝብ ለከፋ ጉዳት ዳርገዋል። በተጨማሪም በዘረፉት ሀብት አሁንም ድረስ አገርን ለማፍረስ እያዋሉት መሆኑ በእጅጉ ያሳዘነው ሶዴፓ እራሱን መለወጥና ያለፈውን መካስ እንዳለበት አምኖ እንቅስቃሴ ጀምሯል።

በዚሁ መሰረት እንደ ሀገር የተፈጠረውን ለውጥና የክልሉ ህዝብ በተጠናከረ መልኩ የጀመረውን ትግል እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ከአንድ አመት በፊት ሶዴፓ እራሱን ለማደስና የተቋቋመለትን ዓላማ በነፃነት ተግባራዊ ለማድረግ የጀመረው ትግል ፍሬ አፍርቶ እነሆ ዛሬ በክልሉ የተሻለ ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር ከማስቻሉም በላይ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ከምንጊዜውም በላይ እየተፋጠኑ ይገኛሉ። የክልሉ ህዝብም ሶዴፓ ከበፊቱ በመማር የጀመረውን ለውጥ እያደነቀና ለውጤታማነቱም ከፓርቲው ጎን በመሆን ድጋፉን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።

ሶዴፓም ውስጣዊ ጥንካሬውን በማጎልበትና እንደ ሃገር የተጀመረው ለውጥ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ህዝቡን ለመካስ የላቀ ጥረት እንዲሁም ከምንጊዜውም በላይ የራሱን ጉዳይ በራሱ እየወሰነ ስኬታማ እንቀስቃሴ እያደረገ ይገኛል።

ይሁንና አንዳንድ በለውጡ ጥቅማቸውን ያጡ አካላት ከዚህ ቀደም በፓርቲያችንና በህዝባችን ላይ ሲያደርሱት በነበረው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ በደል ሳይፀፀቱ ዛሬም የእናውቅልሃለን አካሄድና የድሮውን ለመመለስ ተስፋቸውን በተለያየ መንገድ እየገለፁ ይገኛል። እነዚህ አካላት ባለፉት 27 አመታት ክልላችንን ለችግር ዳርጎ የነበረው አካሄድ ዳግም እንዲመለስ ሶዴፓ መቼም እንደማይፈቅድ ግልፅ ሊሆንላቸው ይገባል። ለፓርቲያችንና ለህዝባችን የሚጠቅመውንም ጠንቅቀን የምናውቅና ቅንነት የጎደለው ምክር የምንሻ አለመሆናችንን ሊገነዘቡት ይገባል።

በተጨማሪም በሶማሌና በአፋር ክልሎች አዋሳኝ አከባቢዎች አገራዊውን ለውጥ ለማዳናቀፍ ሌት ተቀን በሚጥሩ አካላት ህቡዕ እንቅስቃሴ የተፈጠረውን ችግር በህገ-መንግስቱ መሰረት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሶዴፓ ቁርጠኛ መሆኑን ይገልፃል።

በሌላ በኩል ባለፉት 27 አመታት የበላይነት ይዘው የነበሩ የልዩነትና ጥላቻ ትርክቶችን፣ የብሔር ፅንፈኝነትንና አጋር ድርጅቶችን አግላይ አካሄዶችን በሚፈታ መልኩ ኢህአዴግ የጀመራቸውን ለውጦች ሶዴፓ ያደንቃል። በተያያዘም ኢህአዴግ ባለፉት አመታት የነበሩትን ስኬቶች ለማስቀጠል፣ የነበሩትን ስህተቶች ለማረምና አዳዲስ እድሎችን ለመፍጠር እንዲሁም አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር በሚያስችል መልኩ እራሱን ለመለወጥና አጋር ድርጅቶችንም ለማቀፍ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ እራስን በራስ ከማስተዳደር ህገ መንግስታዊ ስርዓትና ከምንከተለው የፌዴራል ስርዓት ጋር የማይቃረን፣ አሃዳዊ ስርዓት የመፍጠር ዓላማ የሌለውና ለሀገራችን ወቅታዊ ችግሮች ፍቱን መድኃኒት መሆኑን ሶዴፓ ያምናል።

በመሆኑም የበለፀገችና በህዝቦች መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነት ያረጋገጠች ጠንካራ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እውን የማድረግ ራዕይን ለማሳካት ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር፣ ተባብሮ መስራት፣ የህዝቡን የሰላም፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ በቅንነት እየመለሱ መሄድና ሀገራዊውን ለውጥ በጠንካራ መሰረት ላይ ማኖር ወሳኝ መሆናቸውን በማመን የሶዴፓ ምርጫ የመተባበር፣ የመተጋገዝ፣ የመዋደድና የእውነተኛ ህገ-መንግስታዊና ህብረ-ብሔራዊ ፌዴራላዊ ስርዓት እንጂ ወደ ነበረው በደል፣ ግፍና ትርምስ የሚመልሰን ማንኛውም ህልም ሶዴፓ ዘንድ ቦታ የሌለው መሆኑን እንገልፃለን።

በህብረት የአገራችን መፃኢ እድል ብሩህ ነው!!!

ሶዴፓ ማዕከላዊ ጽ/ቤት
ጥቅምት 10/2012 ዓ.ም
ጅግጅጋ
... See MoreSee Less

View on Facebook

የአስም በሽታ ምንድነው? ምክንያቱስ፣ ምልክቶቹስ፣ እንዴት መከላካል ይቻላል? ለሚሉና ለተያያዥ ጥያቄዎች ምላሽ እንሆ
*************************
(ኢፕድ)
አስም ክረምቱ አልፍ መስከረም እና ጥቅምት አካባቢ የአስም በሽታ የሚበረታበት ወቅት ነው:: የዚህ በሽታ ስርጭት በአገራችን ውስጥ በትክክል ባይታወቅም በአሜሪካ ግን ከአጠቃላይ የአገሪቷ ህዝብ ውስጥ 7% የሚሆኑ ሰዎች በዚህ በሽታ የተጠቁ ናቸው፡፡ ቁጥራቸው አነስተኛ ያልሆኑ ሰዎችም በዚህ በሽታ ምክንያት በየዓመቱ ህይወታቸው ይቀጠፋል፡፡

የአስም በሽታ ምንድነው? የዚህ በሽታ አምጪ ምክንያትስ ምንድነው?
የአስም በሽታ አየርን ወደ ሳምባ የሚወስድ የአየር ቧምቧን እና በሳምባ ውስጥ የሚገኙ ትናንሽ የአየር ቱቦዎችን የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡ ይህ በሽታ የሚከሰተው የእነዚህ የአየር ቱቦዎች/ ቧምቧዎች ስፋት (ዲያሜትር) ሲቀንስና አየርን በትክክል ማመላለስ ሲያቅታቸው ነው፡፡ የእነዚህ የአየር ቧምቧዎች ስፋትም የሚቀንሰው አለርጂ (allergy) ሲኖረው እና ወፍራም ፈሳሽ (Mucus) ጤናማ ሰው ከሚያመነጨው በላይ ሲያመነጩ ነው፡፡ የአየር ቧምቧ ሲጠብ እና በዚህ ወፍራም ፈሳሽ (Mucus) ሲሞላ አየር ወደ ውስጥ መግባት እና መውጣት አይችልም። ከዚህም የተነሳ በዚህ ችግር የተያዙ ሰዎች የተለያዩ ምልክቶችን ማሳየት ይጀምራሉ፡፡

ለአስም በሽታ ያጋልጣሉ ከሚባሉ ነገሮች መካከል፣
በአስም በሽታ የተያዘ የስጋ ዝምድና መኖር ሌሎች አለርጂ በሽታዎች መኖር (እንደ የቆዳ እና የሳይነስ አለርጂዎች) የሰውነት ክብደት ከመጠን በላይ መጨመር፣ ሲጋራ ማጨስ እና ሲጋራ በሚያጨሱ ሰዎች አጠገብ በመገኘት ለሲጋራ ጭስ መጋለጥ (Passive Smokers) በሥራ ላይም ሆነ በሌላ ምክንያት ከተለያዩ ፋብሪካዎች ለሚመነጩ ኬሚካሎች መጋለጥ

የበሽታው ምልክቶች፣
ከዚህ በሽታ ምልክቶች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ሳል (በተለይ ማታ ማታ እና በብርድ ወይም በቅዝቃዜ ጊዜ)፣ አየር ሲተነፍሱ የማንኮራፋት ድምፅ ማሰማት፣ መተንፈስ አለመቻል ወይም የአተነፋፈስ መቆራረጥ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ የዚህ በሽታ አስከፊነት ከሰው ሰው ይለያያል፡፡በአንዳንድ ሰዎች ላይ ቀላል ሆኖ ትናንሽ ምልክቶችን ብቻ የሚያሳይ ሲሆን በሌሎች ላይ ደግሞ መተንፈስ አቅቷቸው ከመደበኛ ሥራቸው እስከ መቅረትና ሕይወት እስከመቅጠፍ የሚያደርስ ነው። ይህ የአስም በሽታ የሚያሳየው ምልክት ብዙውን ጊዜ ቀጣይነት ያለው ሳይሆን በመሀል እረፍት እየሰጠ ሌላ ጊዜ እየባሰ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ምልክቱ እየቀነሰ የሚታይ ነው፡፡

የአስም በሽታና ሊያስነሱ የሚችሉ ሁኔታዎች፣
የአየር ቧምቧዎችንም ከሰውነታችን አካላት ውስጥ አንዱ በመሆናቸው ወደ ሰውነታችን ባዕድ ነገሮች ሲገቡ የመቆጣት ባህሪ ያሳያሉ፡፡ በተለይም ደግሞ የአስም በሽታ ያለባቸው ሰዎች ወደ ሰውነታቸው ባዕድ ነገሮች ሲገባ የአየር ቧምቧቸው ይቆጣል፤ የመተንፈሻ አካል ይጠባል፤ አክታ መሳይ ነገር ይለቃል።

ሰውነታቸው የሚከላከሏቸው ወይም የሚጠሏቸው ነገሮች አለርጂ ይባላሉ። የጤናማ ሰዎች የአየር ቧምቧ አለርጂ ቢያጋጥመውም ምንም አይነት የቁጣ ወይም የመለወጥ ነገር አያሳዩም ፡፡ የአስም በሽታ ያለባቸው ሰዎች አካል ግን ይቆጣል፤ በበሽተኛው ላይም ህመም ያስከትላል፡፡

ሰውነታችንን ከሚያስቆጡ ነገሮች ውስጥ ጥቂቶቹ፣ ቀዝቃዛ አየር፣ ደረቅ አየር፣ ልዩ ልዩ የአበባ ብናኞች እና በአየር ውስጥ የሚገኙ ጥቃቅን ነገሮች፣ ከባድ ሽታ (ጠረን ወይም ጥሩ መዓዛ)፣ ሲጋራ ማጨስ ወይም ለሲጋራ ጭስ መጋለጥ፣ አቧራ፣ እንደ ሳል እና የሳምባ ኢንፌክሽን ያሉ የአየር ቧምቧን የሚያጠቁ በሽታዎች፣ የአእምሮ ጭንቀት (stress)፣ የሚነድ ማገዶ ጭስ፣ የቤት እንስሳት ጠረን፣ ለሌሎች በሽታዎች የሚሰጡ አንዳንድ መድኃኒቶች፣ የአካል እንቅስቃሴ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ይህንን በሽታ እንዴት መከላከል ይቻላል?
የአስም በሽታ የሚያስነሱ ነገሮችን ማንሳት ያስፈለገበትእና መከላከሉ ላይ ትኩረት የተደረገበት ዋነኛው ምክንያት በሽታውን የሚፈውስ ፍቱን መድኃኒት ባለመገኘቱ ምክንያት ነው፡፡ ነገር ግን በሽታው እንዳይነሳ እና ሰውን እንዳይጎዳ ማድረግ ይቻላል፡፡ በሽታው ከመቀስቀሱ በፊት ከሚደረግ ጥንቃቄ ባሻገር ከተነሳም በኋላ ለአጭር ጊዜ እና የረጅም ጊዜ የአስም ምልክቶችን የሚቆጣጠሩ መድኃኒቶች (controllers) አሉ፡፡

እነዚህ መድኃኒቶች በአይነታቸው እንደ በሽታው ክብደት የሚለያዩ እና በቀጣይነት ወይም በሽታው በሰውየው ላይ በሚነሳበት ጊዜ ብቻ የሚወሰዱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም የአስም በሽታ ከጤና ባለሙያ የሚታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ በመውሰድ በሽታውን መቆጣጠር ይቻላል፡፡

ከእነዚህ መድኃኒቶች በተጨማሪ በዚህ በሽታ የተያዙ ሰዎች በሽታውን የሚያስነሱባቸው ነገሮችን ካወቁ እነዛን ነገሮች ማስወገድ ወይም በዛ አካባቢ መገኘት የለባቸውም፡፡ ለምሳሌ፡ - በሽታው ቀዝቃዛ አየር የሚጠላ ከሆነ በአፍ ላይ ሻሽ ወይም ሌላ መልበሻ አፍ ላይ አድርጎ መጓዝ በጣም ይረዳል። በሽታውን የሚያስነሳብን ነገር አውቀን እራሳችን ከሚያስነሳው ነገር መከላከል/መጠበቅ፤ ከባድ መድኃኒት ከመውሰድ እና ሆስፒታል ከመተኛት ህመምተኛውን ይታደገዋል። ህመምተኛው ሲጋራ የሚያጨስ ከሆነ መተው እንደዚሁም ሲጋራን ከሚያጨሱ ሰዎች መራቅ አስፈላጊ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን ምን እንደሚያስነሳባቸው ስለማያውቁ በሽታውን ከሚቀሰቅስባቸው ነገር ለመራቅ ሲቸገሩ ይታያሉ፡፡

የአስም በሽታ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው መተላለፍ ይችላልን?
በማህበረሰቡ ውስጥ አንዳንድ ጊዜ የአስም በሽታ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው በሳል ይተላለፋል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ይህ ስህተት ሲሆን የአስም በሽታ ከአንድ ህመምተኛ ወደ ሌላ ሰው በማንኛውም መንገድ አይተላለፍም፡፡ በደም ስር (Ge¬netics) ግን በተወሰነ ያህሉ ከወላጅ ወደ ልጅ ሊተላለፍ ይችላል፡፡ ይህ ማለት ግን አባት እና እናት የአስም በሽታ ሲኖርባቸው ልጃቸው በበሽታው ይያዛል ማለት ሳይሆን ይህ ህጻን ይበልጥ ለአስም በሽታ የመጋለጡ እድል ከፍተኛ ነው ማለት ነው፡፡

ከአስም በሽታ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች ምንድናቸው?
የአስም በሽታ ለሌለባቸው ሰዎች እንደ ቀላል ሊታዩ የሚችሉ እንደ ሳል (ጉንፋን) ያሉ የአየር ቧንቧዎች ኢንፌክሽኖች የአስም በሽታ ያለበትን ሰው የያዙ እንደሆነ በጣም ጠንተውበት በአስጊ ደረጃ ላይ ማድረስ ይችላሉ፡፡ ይህ የሚሆነውም የአስም በሽታ የሚቀስቅስ/ እንዲከፋ የሚያደርግ ችግር ስላለባቸው ነው፡፡
የአስም በሽታ በህክምና ባለሙያ የተሰጠውን የአስም መድኃኒት በአግባቡ አለመውሰድ ወይም ሐኪም ቤት ሄዶ አለመታከም በደቂቃዎች ወይም በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የአተነፋፈስ ሥርዓት እንዲዳከምና ታማሚው በበሽታው እንዲሰቃይ ያደርጋል፡፡አልፎ ተርፎም በቀላሉ ነፍስ ሊቀጥፍ ይችላል፡፡
ስለዚህ የአስም በሽታ ምልክቶችን በሰውነት ላይ ካዩ ወደ ሐኪም ቤት በመሄድ አስፈላጊውን ህክምና በማግኘት እነዚህን ችግሮች ማስወገድ ይቻላል፡፡

ምንጭ አዲስ ዘመን ቅዳሜ ጥቅምት 8 ቀን 2012 ዓ .ም የዘመን ሃኪም ዓምድ

ለአዳዲስ መረጃዎች በለውጥ ሂደት ውስጥ ያለውን አዲስ ዘመን ጋዜጣን ይወዳጁ!
... See MoreSee Less

View on Facebook

National-News

Editorial-View-Point

Ethiopian Herald

Business-Market

Society

Development

Art-Culture

Sport

Nobel Peace Prize A big inspiration and a boost to Ethiopia’s...

Back in 1991, soon after the rebel forces in Eritrea and Ethiopia took power in Asmara and Addis Ababa respectively, there was widespread speculation...